
የራያ አማራ እና በሰላማዊ ሰልፍ ካስተላለፋቸው መልዕክቶች መካከል:_ “አማራ ነን እንጅ አማራ እንሁን አላልንም!”፣ “ወይ ፍንክች አማራ ወይ ፍንክች አጅሬ፣… ራያ እና ወልቃይት አይደሉም የትግሬ!”፣ “እኛ ወሎ ራያዎች በነጻነታችን እና ማንነታችን አንደራደርም!” ከአሸባሪው ህወሓት ወረራ ነጻ የወጡት የራያ አላማጣ ነዋሪዎች መጋቢት 10/2015 በአላማጣ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ከተላለፉ መልዕክቶች መካከል ይገኙበታል። የራያ እና የወልቃይት አማራ የማንነት ጥያቄዎች አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጣቸውም መጠየቃቸው ታውቋል። በተጨማሪም በማይጨው ታስረው የሚገኙ የራያ አማራዎች እንዲፈቱም ጠይቀዋል።
Source: Link to the Post