“የራያ የማንነት እና የወሰን ጉዳይ የመላው አማራ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ ነው” የአማራ ሚዲያ ማእከል ነሐሤ 01/2014 ዓ.ም ደሴ ኢትዮጵያ የወሎ ራያ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላ…

“የራያ የማንነት እና የወሰን ጉዳይ የመላው አማራ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ ነው” የአማራ ሚዲያ ማእከል ነሐሤ 01/2014 ዓ.ም ደሴ ኢትዮጵያ የወሎ ራያ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ በራያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በደሴ ከተማ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው። በምክክር መድረኩ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የራያ ተወላጆች እና የምሥራቅ አማራ ፋኖ አባላት ተገኝተዋል። የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ከድር ሙስጠፋ የውይይቱ ዓላማ የራያ የማንነት እና የወሰን ጉዳይ የመላው አማራ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ መሆኑን ማስገንዘብ ነው ብለዋል። የወልድያ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አበበ ግርማ የራያ ሕዝብ ለበርካታ ዓመታት በማንነቱ ጫና ሲደርስበት እንደነበር ተናግረዋል። አሁንም በከፋ ችግር ውስጥ መሆኑን ጠቅሰው ነፃነቱ ሊረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የራያ ሕዝብን አንድነት በማጠናከር የሕዝቡን ነጻነት ለመመለስ የወሎ ራያ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ እየሠራ መሆኑን የተናገሩት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር እና የአብን ሊቀመንበር ዶክተር በለጠ ሞላ ኮሚቴውን በማገዝ የራያ ሕዝብ ነፃነቱን እንዲያገኝ በአንድነት መሥራት አለብን ብለዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የወሎ ራያ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ባለፈው አንድ ዓመት ባከናወናቸው ተግባራት እና የወደፊት የትግል አቅጣጫዎች ላይ እየመከረ ነው። አሚኮ

Source: Link to the Post

Leave a Reply