You are currently viewing የሮሃ ሚዲያ የስቱዲዮ ምርቃት በርካታ ተጋባዥ የክብር እንግዶችና ጋዜጠኞች በተገኙበት ተከናውኗል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ/ም           አዲስ አበባ…

የሮሃ ሚዲያ የስቱዲዮ ምርቃት በርካታ ተጋባዥ የክብር እንግዶችና ጋዜጠኞች በተገኙበት ተከናውኗል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ…

የሮሃ ሚዲያ የስቱዲዮ ምርቃት በርካታ ተጋባዥ የክብር እንግዶችና ጋዜጠኞች በተገኙበት ተከናውኗል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የሮሃ ሚዲያ ስቱዲዮ ዛሬ ህዳር 20/2015 አመሻሹን በርካታ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ ፖለቲከኞች፣ የህግ ባለሙያዎች እና መላው የሮሃ ጋዜጠኞች፣ አዘጋጆች እንዲሁም የቀረጻ ባለሙያዎች በተገኙበት ተመርቋል። የሮሃ ሚዲያ ባለቤት ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርጋለች። በንግግሯም ፍቃዱን ለማግኘት የፈጀባቸውን አንድ ዓመት ጊዜ እና በየመካከሉ የገጠማቸውን ፈተና በአሸናፊት ያለፉ የሮሃ ሚዲያ ቤተሰቦችን፣ በውስጥም ሆነ በውጭ የሮሃ ሚዲያ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ያልተቆጠበ ድጋፍ ያደረጉ አካላትን በሙሉ እንዲሁም ጥሪውን አክብረው በምርቃቱ የተገኙትን አመስግናለች። ካደረገች በኋላ ስቱዲዮውን በተጋባዥ የክብር እንግዶች እና በጋዜጠኞች የማስጎብኘት እና የማስመረቅ ስራ ተሰርቷል። በምርቃቱም ፖለቲከኛ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት እና ሌሎች ፖለቲከኞች፣ ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው፣ ጠበቃ አዲሱ ጌታነህ፣ ጠበቃ አዲሱ አልጋው እና የቀድሞ የአባይ ሚዲያ ባልደረቦቿን ጨምሮ ከተለያዩ ሚዲያዎች የመጡ በርካታ ጋዜጠኞች ተገኝተዋል። በምርቃቱ ከተገኙት መካከልም አብዛኞቹ በቀደመውም የህወሓት ኢህአዴግም ሆነ የስም ለውጥ ብቻ ነው ያደረገው በሚል ብዙዎች በሚወቅሱት በብልጽግና ዘመን ለግፍ እስር የተዳረጉ መሆናቸውን በስፍራው የተገኘው አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተመልክቷል። በጉብኝቱ ከተሳተፉ እንግዶችም ብዙዎች ስቱዲዮን እጅግ በጣም ወደውታል፤ አበረታች እና ብዙ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል መሆኑንም መስክረዋል። ከስቱዲዮ ጉብኝቱ በኋላም የእራት ግብዣ ተደርጓል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply