የሮም ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የአጋርነት ደብዳቤ በፖፑ የክርስቲያን አንድነት ፕሬዝደንት በኩል ላከች::ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮህ የፖፕ ፍራንሲስ የክርስቲያኖች አንድነት ፕሬዝዳንት (Pres…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/nb80vJPl6wGAcGm0APBlG731Xb_xLw191RRFdC-CgQtX0-jc_pox2TSYhAsxMqPJqPkN0kQItsdl5peSZB3T2DeQ9HBZRSLBGMBbAh-q_6jyy8eKdKfAf-isujzJ07siB-98XHyge0-lG5qHg8HGMeWot9JPO5YY5zoXd3rs4Jb2zJZfEdIqhkl0_GCMOZJ2JCfElGuIgYn83sPnyfU9Yqnux5ZX70bqIySmUyduJSZV1GMrKh5R2HMcKMZXzv-K49A2DX4IyxfAj0Q_ifoQoBjObJVBy3XshrfchqXQ3c6G-h-BmZt-LAJrhbz2FrL4J8dGDsMazNNl5PJN0S5vqA.jpg

የሮም ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የአጋርነት ደብዳቤ በፖፑ የክርስቲያን አንድነት ፕሬዝደንት በኩል ላከች::

ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮህ የፖፕ ፍራንሲስ የክርስቲያኖች አንድነት ፕሬዝዳንት (President Pontifical Council for Prompting Christian Unity) እንደገለጹት “በተፈጠረው ችግር እና ሁኔታ ጥልቅ ሐዘን የተሰማን ሲሆን ለቅዱስ ሲኖዶስ ያለንን አጋርነት በመግለጽ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለመጠበቅ የሚደረግ ጥረትን በሙሉ እንደግፋለን” ብለዋል::

በመልእክታቸው መጨረሻም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ በለከው የመጀመሪያ መልእክት “አንድም ብልት ቢሣቀይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።”

1ኛ ቆሮንቶስ 12፥26 የለውን ጠቅሰው ሕመማችን ሕመማቸው ክብራችን ክብራቸው መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ እና የቤተ ክርስቲያን አንድነት እናት በምልጃዋ እጅግ የተከበረች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አንድነቷና ደህንነቷ እንዲጠበቅ ታድርግልን ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 03 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply