የሮይተርስ ዜና ወኪል የካሜራ ባለሞያው ኩመራ ገመቹ መታሰሩ ተገለጸ

https://gdb.voanews.com/D589B421-6202-44AF-8CB5-154CE282BAFA_cx0_cy4_cw0_w800_h450.jpg

ሮይተርስ የዜና ወኪል የካሜራ ባለሞያው ኩመራ ገመቹ አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ሐሙስ ታኅሣሥ 15/2013 ዓ.ም መወሰዱንና ለቀጣይ ሁለት ሳምንታትም በእስር እንደሚቆይ ቤተሰቦቹን ጠቅሶ ዘገባ አቅርቧል።

ኩመራ እስካሁን ምንም ዓይነት ክስ እንሳልተመሰረተበና ስላታሰረበት ምክኒያት ቤተሰቦቹ የሚያውቁት ነገር እንደሌለም ሮይተር በመግለጫው አክሏል።

የ38 ዓመቱ ኩመራ ለሮይተርስ የዜና ወኪል የካሜራ ባለሞያ በመሆኑ ከዐስር ዓመት በላይ መሥራቱን የገለፀው ድርጅቱ፤ አርብ ዕለት ያለ ጠበቃ ለጥቂት ሰዓታት ፍርድ ቤት ቀርቦ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀናት የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ በዳኛው ይሁንታ ስላገኘ በእስር እንዲቆይ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

ሮይተርስ የካሜራ ባለሞያውን መታሰር አውግዞ ባወጣው መግለጫ፤ ኩመራ በቁጥጥር ስር የዋለው ሌላው የሮይተርስ የካሜራ ባለሞያ ጢቅሳ ነገሪ ታኅሣሥ 7/2013 ዓ.ም በሁለለት የፌደራል ፖሊስ አባላት መደብደብን ተከትሎ ነው ብሏል።

ኩመራን ወደ ዐሥር የሚጠጉ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ቤቱ በመሄድ በባለቤቱና በሦስት ልጆቹ ፊት በእጅ ካቴና አስረው እንደወሰዱት የገለፀው ሮይተርስ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ምላሽ አለማግኘቱን አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply