
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ከኢፌዴሪ የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራመ፡፡
ተቋማቱ በአዋጅ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በጥራትና በቅልጥፍና በማከናወን የተቋቋሙበትን ዓላማ ከግብ ማድረስ እንዲችሉ በትብብር መስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ የስምምነት ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡
ስምምነቱ ሁለቱም ተቋማት በአዋጁ ከተሰጣቸው ስልጣንና ተግባራት መካከል የሚወራረሱ ተግባራት በመኖራቸው ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን የጋራ ስምምነቱ የስራ ድግግሞሽንና የሀብት ብክነትን ለመቀነስ የሚያስችል እንደሆነ መናገራቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
The post የሰላም ሚኒስቴር እና የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.
Source: Link to the Post