
በትግራይ ውስጥ ሲካሄድ የነበረውን ጦርነት ለማስቆም በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የተደረገው ስምምነት በአሜሪካ ግፊት ህወሓትን ለማዳን የተደረገ ነው ሲሉ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ተናገሩ። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መሪዎች መካከል ስምምነት ተደርጎ ጦርነቱ ከቆመ ከሦስት ወር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እሁድ የካቲት 05/2015 ዓ.ም. ለአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት ቃለ መጠይቅ ነው ይህንን ያሉት።
Source: Link to the Post