የሰላም   እና የሴቶች ሚኒስትር (አሻራ ታህሳስ 24፣ 2013ዓ.ም) ሀ)ሰላም ሚኒስትር…  ከለውጡ በኃላ የተፈጠረ ጭንጋፍ ተቋም ነው፡፡ አፈጣጠሩ አቶ መለስ ፀረ ሙስናን ካዋቀሩበት መንገ…

የሰላም እና የሴቶች ሚኒስትር (አሻራ ታህሳስ 24፣ 2013ዓ.ም) ሀ)ሰላም ሚኒስትር… ከለውጡ በኃላ የተፈጠረ ጭንጋፍ ተቋም ነው፡፡ አፈጣጠሩ አቶ መለስ ፀረ ሙስናን ካዋቀሩበት መንገ…

የሰላም እና የሴቶች ሚኒስትር (አሻራ ታህሳስ 24፣ 2013ዓ.ም) ሀ)ሰላም ሚኒስትር… ከለውጡ በኃላ የተፈጠረ ጭንጋፍ ተቋም ነው፡፡ አፈጣጠሩ አቶ መለስ ፀረ ሙስናን ካዋቀሩበት መንገድ ጋር ይመሳሰላል፡፡ አቶ መለስ ከኢሳያስ ጋር በኢኮኖሚ ውድድር ሲቃቃሩ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጦርነት አስጀመሩ፡፡ በጦርነቱ 100ሺ ሰው አለቀ፡፡ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ቢጠናቀቅም ኢትዮጵያ ባድሜንም አላገኘችም፡፡ ፖለቲካዊ ድሉ ከኢሳያስ እጅ ገባ፡፡ አንድ ነገር ግን ሆነ፡፡ ህወኃት ተከፋፈለ፡፡ የስየ አብርሃ ቡድን ተመቶ አቶ መለስ እስከ 2004 ገና ገና ሆነው ወጡ፡፡ ለገናናነታቸው ማስጠበቂያ ፀረ ሙስና ተቋምን ለእነስየ መወንጀያ አድርገው አዋቀሩት፡፡ ስየ አብርሃ እና ታምራት ላይኔ የፀረ ሙስና ተቋም እንደተመሰረተ የስራ ማስጀመሪያ አደረጋቸው፡፡ ተቋምም የፖለቲካ አመለካክቱ ላላማረው መክሰሻ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ወደ ሰላም ሚኒስትር እንምጣ፡፡ ሙፈሪያት የአቶ ደመቀን ቦታ እንድትይዝ አብይ አህመድ ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን የአቶ ደመቀ ሀይል የሚነካ አልሆነምና አቶ ደመቀ እንደ ሀይለማርያም ደሳለኙ ዘመን ምክትል ሆነው ቀጠሉ፡፡ ከዚያማ አብይ ስልጣንን በታዛዣቸው ሙፈሪያት ስር ለማከማቸት የሰላም ሚኒስቴር ብለው ፈጠሩ፡፡ በሰላም ሚኒስትር ስር ብሄራዊ ደህንነት፣ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህነት፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ የሀገሪቱ መከላከያ የመረጃ ክንፍ ሁሉ በሰላም ሚኒስትር ስር ሆነ፡፡ በእርግጥ በሀላፊነት ከምክትል ጠቅላይሚኒስትርነት ይልቅ የሰላም ሚኒስቴርነት ስልጣን ይበልጣል፡፡ ታዲያ ምን ያደርጋል ወይዘሮ ሙፈሪያት የተፈናቀለ እና የተጎዳ ሲያዮ ሲለቅሱ፣ የተጣላ ሲያገኙ የሀገር ሽማግሌ ይዘው ሲያስታርቁ፣ አነብናቢ ምሁራንን ይዘው ሰላም አስፈላጊ ነው ብለው ሲሰብኩ ሁለት ዓመት አለፋቸው፡፡ የሰላም ሚኒስትር ከአንድ ተራ የመረዳጃ ማህበር ያነሰ ሚና ኖረው፡፡ ችግርን ቀድሞ መተንተን እና መፍትሄ ከመስራት ይልቅ አንደበታዊ ስብከት በመስበክ ሰላም ሚኒስትር የሀይማኖት ተቋማት የስብከት ጉባዔ መሰለ፡፡ ሰላም ሚኒስትር ከምክር፣ ሰው በጅምላ ከተጨፈጨፈ በኃላ ከማቃበር፣ ከተፈናቀለ በኃላ ምግብ ከማድረስ የዘለለ ሚና የሌለው ደካማ የሲቪክ ማህበር ሆኖት አረፈ፡፡ ህወኃት ምሽግ ሲቆፍር፣ ሚሳኤል ሲታጠቅ ሰላም ነው ብሎ ፀጥ ያለው ሰላም ሚኒስቴር፣ ኦነግም በተመሳሳይ በገዥው መንግስት ድጋፍ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ታጥቆ ከኮንሶ እስከ ወለጋ፣ ከሀረር እስከ መተከል ንፁሃንን ሲጨፍጭፍ ሰላም ሚኒስቴር ሰላም አስፈላጊ ነው ብሎ ይተኛል፡፡ ለ) የሴቶች እና ህፃናት ሚኒስቴር የሴቶች ሚኒስትር ፖለቲከኞች ለዲፕማሲ መሸቀያ የፈጠሩት ሽባ ተቋም ነው፡፡ ስራዓተፆታ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ነው፡፡ የዓለምአቀፍ ስምምነቶች ሁሉ መገምገሚያ መስፈርት ነው፡፡ ሴቶች ላይ የሰራ የበጀት ድጎማም አለ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም ከካቢኔ 50% ሴቶች አድርጌያለሁ፡፡ ፕሬዜዳንትም ሴት ናት፡፡ ቀጣይ ሴት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ይኖረናል እያሉ በሞቅታ አስወሩ፡፡ የተወሰነም ቢሆንም የዲፕሎማቲክ ድል ተጎነጩበት፡፡ ሴቶች በአብዛኛው ለስላሳ እና የአስታራቂነት ባህሪ ስላላቸው ዶክተር አብይንም አለመጎርበጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሴት ሴት እንዲሉ አደረጋቸው፡፡ ንጉስ ለመሆንም ተመቻቸው፡፡ የሴቶች ሚኒስቴርም “እኔ ከባሌ እኩል ነኝ፣ ባሌ እንጀራ ይጋግር፣ ባሌ ካልሲየን ይጠብ” የሚል አይነት ዘመቻ የባህል ልብስ እየለበሱ ከማወጅ ውጭ ሌላ ወፍ የለም፡፡ እርጉዞች ሆዳቸው ሲተረተር፣ ህፃናት ኩላሊታቸው ወጥቶ ሲበላ፣ እናቶች ጡታቸው ሲቆረጥ የሴቶች ሚኒስቴር ዘመቻው ሚስት ከባሏ እኩል ናት የሚል ሞኝ ሞኝ ሀሳብ ብቻ ያመነዥካሉ፡፡ በመተከል ብቻ 20 ሺ ህፃናት፣ ሁለት ሺ ነፍሰጡር ሴቶች፣ 400 አራሶች ተፈናቅለዋል፡፡ የሴቶች ሚኒስቴር የሚባለው አስመሳይ ተቋም እንኳን ከጥቃት ሊያድን ሂዶ አልጠየቃቸውም፡፡ እንደ ሰላም ሚኒስቴር እና እንደ ሴቶች ሚኒስቴር አሳፋሪ ተቋም ያለ አይመስልም፡፡ ከጌዲዮ እስከ ቡራዮ፣ ከመተከል እስከ ጉራፈርዳ ንፅሃንን ሲጨፈጨፉ እነዚህ ተቋማት መንግስት ላይ ከንፈር የመምጠጥ ሞራል እንኳን አላገኙም፡፡ የተቋማት ውድመት እና አድርባይነት የግጭቶች ሁሉ ማዕከል ነው፡፡https://youtu.be/9frOfC4jlZE

Source: Link to the Post

Leave a Reply