የሰላም ወሬና የመንግሥትና የህወሓት ምልልስ

https://gdb.voanews.com/01a10000-0aff-0242-250d-08da808fbda4_tv_w800_h450.jpg

በኢትዮጵያ መንግሥት የተቋቋመው የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ ወደ ተኩስ አቁም ስምምነት ሊያደርስ የሚችልና ለቀጣይ የፖለቲካ ውይይቶች መሠረት የሚጥል የሰላም ምክረ ሃሳብ ማፅደቁን መንግሥት ገልጿል።

ሃሳቡን በተመለከተ ኮሚቴው ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ማብራሪያ መስጠቱን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የትግራይ ክልልን ጨምሮ በሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች ሰብዓዊ ድጋፍ አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ እንዲደርስና የመሠረታዊ አገልግሎቶችን ሥራ እንደገና ለማስጀመር የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር በአጭር ጊዜ ውስጥ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ላይ መድረስ እንደሚገባም ተገልጿል።

ይህን መግለጫ ተከትሎ የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በትዊተር በሰጡት ምላሽ የመንግሥት ኃይሎች “በተለያዩ ግንባሮች ኃይላችንን እየተነኮሱ ባሉበት ወቅት” የሰላም ኮሚቴ የሚባለው አካል “ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ በማሳሳት የተለመደ የማደናገሪያ ጨዋታው ተጠምዷል” ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply