#የሰማእታት_ፋኖ_መታሰቢያ_በደላንታ_ወገልጤና_ተደረገ! ጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በዛሬው ቀን በርካታ የወገልጤና ከተማ ህዝብ በተገኜበት በራያ ግንባር ምሽግ ደ…

#የሰማእታት_ፋኖ_መታሰቢያ_በደላንታ_ወገልጤና_ተደረገ! ጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በዛሬው ቀን በርካታ የወገልጤና ከተማ ህዝብ በተገኜበት በራያ ግንባር ምሽግ ደርምሰው መስእዋትነት የሆኑ የምስራቅ አማራ ፋኖ አባላት “የበጋው መብረቅ” በርካታ ህዝብ እና የፋኖ አባላት በተገኙበት የ40 ቀን መታሰቢያ የሻማ ማብራት ፕሮግራም ተደርጓል። በመታሰቢያ ፕሮግራሙ ላይ የምስራቅ አማራ ፋኖ የደላንታ አካባቢ መሪ ፋኖ ተመስገን አለባቸው ከአካባቢው ህዝብ የአሳምነው ፅጌ ፎቶ ተበርክቶላቸዋል እሳቸውም ለተደረገው ስጦታ አመስግነው መልእክት አስተላልፈዋል “መስእዋትነት የከፈሉት ፋኖወቻችንን አላማ ሁላችንም ከግብ የማድረስ ግዴታ አለብን ትግላችን የሚቆመው ያለ ህግ የተወሰደብን የራያ እና የወልቃይት ነባር እርስታችን በህግ ማእቀፍ ወደ ቀድሞው የአማራ ግዛት ሲመለስ ብቻ ነው” በማለት መልእክት አስተላፈዋል። ክብር ለአማራ ፋኖ ጥቅምት 26/5015 ዓ.ም © Yergalem Tadesse ላኮመልዛው ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply