የሰሜን ሜጫ ወረዳ የአብን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አመራሮች የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በሚል ወደ ደቡብ ሜጫ ባቀኑበት ተይዘው ከሰዓታት የእስር ቆይታ በኋላ መለቀቃቸው ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

የሰሜን ሜጫ ወረዳ የአብን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አመራሮች የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በሚል ወደ ደቡብ ሜጫ ባቀኑበት ተይዘው ከሰዓታት የእስር ቆይታ በኋላ መለቀቃቸው ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

የሰሜን ሜጫ ወረዳ የአብን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አመራሮች የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በሚል ወደ ደቡብ ሜጫ ባቀኑበት ተይዘው ከሰዓታት የእስር ቆይታ በኋላ መለቀቃቸው ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የምዕራብ ጎጃም ዞን የአብን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አሸናፊ አካሉ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል ያደረሱት መረጃ እንዳመለከተው ዛሬ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጠዋት ላይ ከሰሜን ሜጫ ወረዳ የተነሱ 3 የወረዳው የአብን አመራሮች ለልምድ ልውውጥ በሚል ወደ ደቡብ ሜጫ ወረዳ አቅንተዋል። አቶ አሸናፊ እንደገለፁት ጉዞ ያደረጉት አመራሮችም የሰሜን ሜጫ ወረዳ የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር ጌታነህ ዘገዬ፣ የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊው መምህር አንዳርጌ ዘገዬና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው መምህር ሙሉ ሰው የኔአባት ናቸው። ጠዋት 3 ሰዓት አካባቢ ደቡብ ሜጫ ወረዳ የደረሱት አመራሮቹ ከወረዳው አመራሮችና አባላት ጋር ተገናኝተው የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ሁኔታ ክልከላና እስር እንደገጠማቸው ተገልጧል። እንደ አቶ አሸናፊ መረጃ ክልከላ ከማድረግ አልፈው በፖሊስ እንዲታሰሩ የተደረጉት በደቡብ ሜጫ ወረዳ የብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ጋሻው ተናኘ ትዕዛዝ ነው። ይሁን እንጅ በተደረገው ጥረት ከሰዓታት የእስር ቆይታ በኋላ ከቀኑ 7 ሰዓት አካባቢ የተፈቱ መሆናቸው ተገልጧል። ለሰዓታት በእስር ላይ የቆዩትን የወረዳው የአብን አመራሮችንና የደቡብ ሜጫ የብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊን አድራሻ እንዳገኘን ምላሻቸውን አካተን የምንመለስ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply