የሰሜን ምስራቅ ኒውዮርክ ከተማ በሬክተር ስኬል 4.8 በተገመተ የመሬት መቀጥቀጥ መመታቱ ተገለፀ፡፡

8.3 ሚሊዮን ህዝብ በሚኖርበት ከተማ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማየታወቅ ርዕደ መሬት ያጋጠመ ሲሆን ምንም ጉዳት ግን አላደረሰም፡፡

በሰሜን ምስራቅ ዩኤስ አርብ ጠዋት ጀምሮ በ4.8 በሬክተር ስኬል የተመዘገበ ርዕደ መሬት ማጋጠሙን ዩኤስ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አስታውቋል፡፡

ይህ ርዕደ መሬት በቦስተን እና ፊላደልፊያ መካከለም ባለው የአትላንቲክ የባህር ዳርቻ ላይ መከሰቱን ገልፃል፡፡

በትላትናው ርዕደ መሬት በኒውዮርክ፣ኒውጀርሲ፣ማንሃታን እና ሌሎች አምስት አካባቢዎች ላይ የተሰማ ሲሆን 45 ሚሊዮን ህዝብ በድንጋጠየ ውስጥም ቆይቷል ተብሏል፡፡

ርዕደ መሬቱ በኃላ ምንም ዓይነት ወይንም በትልቅ ደረጃ የሚነሳ ጉዳት ጉዳት አለመድረሱን የኒውዮርክ ከተማ እሳትና አደጋ መከላከል መምሪያ አስታውቋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

መጋት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply