You are currently viewing የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና  ጽሕፈት ቤት የተፈናቃይ ቁጥር በመጨመሩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጉዳዩን በትኩረት እንዲያዩት ጥሪ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት የተፈናቃይ ቁጥር በመጨመሩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጉዳዩን በትኩረት እንዲያዩት ጥሪ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት የተፈናቃይ ቁጥር በመጨመሩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጉዳዩን በትኩረት እንዲያዩት ጥሪ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 18 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት በየጊዜው የተፈናቃይ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ጉዳዩ የሚመለከተው ሁሉ ለችግሩ ትኩረት በመስጠት መፍትሄ ሊሰጥ እንደሚገባ ጥሪ አቅረቧል። የተቋሙ ኃላፊ አቶ አበባው መሰለ እንደገለጹት ደብረ ብርሃንን ጨምሮ በዞኑ ባሉ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ጠቅላላ እስካሁን ያለ ነባር ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ተፈናቃዮች በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ያሉ 26 ሺህ 239 በማኅበረሰቡ ውስጥ የተጠለሉ 5 ሺህ 251 በአጠቃላይ 76 ሺህ 490 እንዳሉ ተናግረዋል። ከነዚህ ተፈናቃይች በተጨማሪ ከአዲስ አበባ ዙሪያ:_ 1) በዚህ ሳምንት የመጡ 6 ሺህ 210 ፤ 2) ከምስራቅ ወለጋ ባኮ ዞን አኖ ከተማ የመጡ 2 ሺህ 921 ሲሆኑ በጠቅላላ በዞኑ የተጠለሉ 85 ሺህ 621 የደረሰ ሲሆን ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ በእጅጉ አሳሳቢ እየሆነና አስከፊ ደረጃ ላይ እየደረሰ መምጣቱን ገልጸዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ በቂ ምግብ እና መጠለያ ባለመኖሩ ጉዳዩ ከተቋሙ አቅም በላይ እየሆነ በመምጣቱ በየደረጃው የሚገኘው የመንግሥት አካል ዘላቂ መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚገባ ዛሬ ከሚዲያወች ጋር በነበራቸዉ ቆይታ መልእክት አስተላልፈዋል። ዘገባው የሰሜን ሸዋ መ/ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply