የሰሜን ኢትዮጵያውን ግጭት በአስቸኳይ ማቆም የደቡብ አፍሪካው የሰላም ንግግር ቀዳሚ ጉዳይ እንዲሆን ተጠየቀ

https://gdb.voanews.com/03990000-0aff-0242-860f-08dab7bbb714_tv_w800_h450.jpg

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሃት በደቡብ አፍሪካ በሚያደርጉት የሰላም ንግግር በቅድሚያ “ግጭቱን በአስቸኳይ የማቆም” ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ዩናይትድ ስቴትስ ጥሪ አቀረበች። 

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን፣ “ግጭቱን በአስቸኳ ማቆም” የመጀመሪያው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆን አለበት ብለዋል፡፡ 

ከብሊንከን ጋር የሚመሳሰል መልዕክት ያስተላለፉት ቃል አቀባያቸው ኔድ ፕራይስ በበኩላቸው የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሃመር ንግግሩ ግጭቱን በአስቸኳይ ለማቆም እና ለሌሎችም በርካታ ችግሮች እልባት ለማስገኘት እንደሚረዳ ያላቸውን ተስፋ መግለጣቸውን ትናንት በሰጡት መግለጫ ጠቅሰዋል። 

ለመገናኛ ብዙኃን ዝግ የሆነውን የሰላም ንግግር በተመለከተመተ ስለ ንግግሩ አጀንዳዎችም ይሁን ስለሂደቱ ከዋነኛው አደራዳሪው የአፍሪካ ሕብረት ተጨማሪ እስካሁን ሌላ ማብራሪያ አልተሰጠም፡፡ 

Source: Link to the Post

Leave a Reply