ኪም ጆንግ ኡን ለሀገሪቱ ከፍተኛ አመራሮች ባደረጉት ንግግር ሰሜን ኮሪያ የምግብ እጥረት እንደገጠማት እና በባለፈው ዓመት በተከሰቱ የጎርፍ እና የአውሎ ንፋስ አደጋዎች የተነሳ የግብርናው ዘርፍ መዳከሙን ገልጸዋል፡፡
በእህል ግብዓት እጥረት የተነሳ በሰሜን ኮርያ 1 ኪሎ ግራም ሙዝ እንኳን እስከ 45 ዶላር እንደሚሸጥ ሲገለጽ የምግብ ምርቶች ማዳበርያ እና ነዳጅም ከቻይና እንደሚገቡ እና ሀገሪቱ በቻይና ላይ ጥገኛ እየሆነች እንደመጣች ተነግሯል፡፡
ሰሜን ኮሪያ ባወጣችው የኒኩሌር መርሐ ግብር የተነሳ የዓለም ዓቀፍ ማዕቀቦች እንደተጣለባት ሲታወስ አሁን ላይ ሕዝቦቿ በከባድ የምግብ እጥረት ውስጥ መግባታቸው ታውቋል፡፡
ዘገባው፡- የቢቢሲ ነው
ቀን 10/10/2013
አሐዱ ራድዮ 94.3
The post የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን ሰሜን ኮርያ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማት አምነዋል፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.
Source: Link to the Post