የሰሜን ወሎ፣ አጎራባች ዞንና ክልሎች ተፈናቃዮች በደሴ

https://gdb.voanews.com/bad93f0b-5288-4232-ba5a-adda8ed96dc3_tv_w800_h450.jpg

በሰሜን ወሎና በአጎራባች ዞንና ክልሎች ህወሓት ቀሰቀሰው ባሉት ግጭት ሳቢያ ተፈናቅለው ወደ ደሴና አካባቢዋ የመጡ ተፈናቃዮች ከ350 ሽህ ማለፋቸውን የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ 

የዞኑ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በተፈናቃዮችና እየተሰጠ ባለው ሰብአዊ ድጋፍ ዙሪያ ለአገር ውስጥና ለውጭ አገራት መገናኛ ብዙኃን ተወካዮች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ 

በርካታ ተፈናቃዮች የተጠለሉባቸው ት/ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራ በቅርቡ ስለሚጀምሩ ለተፈናቃዮቹ የካምፕ ግንባታ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡ 

Source: Link to the Post

Leave a Reply