የሰራተኞቹን ነፍስ ለማዳን እርብርብ እየተደረገ ነው፡፡በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ተስፋዬ ወፍጮ ቤት እየተባለ በሚጠራ አካባቢ እየተገነባ ባለ ህንጻ የአፈር ናዳ መከሰቱ ተነገረ፡፡…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/dUg9__5IadC0O4c0epA_Ok5EAHZuAUfDOA2cVBIjTJ3sZ4ZuJoZ6acxfYX0j_jjccq5HQJHEXX2OMuOLRMXJpNubMC2Wclq3ifiwkGcWeo3ChtlgiN2JUsDt4_JIrlVj_P_sDWoZbLvsVZkXT0ZqQZV_yBp2QKolrLb49Bh2AArVvjz1PFDGWZTOKVJftC1Y5K1jEwIYc2byFyNGM5m2i-EWztWEOpwkedO03mMXI6sHLJ_gJRfsAj9iZaJHbJ48xxI2o57WqLhyYoEXuKEzZyKbYuft1TzfX8szLAVqDSj9-qzYL4cRyhIX34SsQ3UAr8Q5l-oKuJcWnErxeWPTdg.jpg

የሰራተኞቹን ነፍስ ለማዳን እርብርብ እየተደረገ ነው፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ተስፋዬ ወፍጮ ቤት እየተባለ በሚጠራ አካባቢ እየተገነባ ባለ ህንጻ የአፈር ናዳ መከሰቱ ተነገረ፡፡

ህንጻ ለመገንባት የአፍር ቁፋሮ እያደረጉ የነበሩ በርካታ ሰራተኞች የአፍር ናዳው እንደተናደባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለጣበያችን ተናግረዋል፡፡

ከአፈር ናዳው እስካሁን ድረስ አንድ ሰው ብቻ ማውጣት እንደተቻለ የገለጹት ነዋሪዎቹ በቦታው ያለው ነገር የሚያሳዝን ነው ብለዋል፡፡

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ሰራተኞች ባሁኑ ሰአት በቦታው መገኝታቸቀው የተነገረ ሲሆን ሰራተኞቹን ለማዳን ብርቱ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

የአፈር ናዳው የደረሰው ህንጻው ከህንጻው አጠገብ ባሉ መኖርያ ቤቶች መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply