የሰቆጣ ከተማ፣የኮረምና የወፍላ ወረዳ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰቆጣ ከተማ ዛሬ ታህሳስ…

የሰቆጣ ከተማ፣የኮረምና የወፍላ ወረዳ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰቆጣ ከተማ ዛሬ ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ.ም በተካሄደው ሰልፍ ዘርን መሠረት ያደረገ ጭፍጨፋን እንቃወማለን፤ ጨፍጫፊዎች በሕግ ሊጠየቁ ይገባል እና ሌሎች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። በተጨማሪም የኮረምና የወፍላ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ ህዝቦች ከህወሃት ጭቆና ነፃ በመውጣታቸው ደስታችን የላቀ ነውም ብለዋል_ሰልፈኞቹ። በተመሳሳይ ዛሬ የኮረምና የወፍላ ወረዳ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ ከተላለፉት መልዕክቶች መካከል ዘርን መሠረት ያደረገ ጭፍጨፋ ይቁም፣ በእጃችን የገባውን ማንነታችንና እድላችንን አሳልፈን አንሰጥም፣ ማንነታችን አማራ ነው የሚሉና ሌሎች መልዕክቶች ይገኙበታል፡፡ በሰልፉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ላስመዘገቡት ድል ምስጋና ቀርቧል፡፡ ምንጭ_አብመድ

Source: Link to the Post

Leave a Reply