የሰባዊ መብት ተቋማት እራሳቸዉን ይገምግሙ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒሲትሩ ጠየቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒሲትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምላሽ እየሰጡ ባሉበት ወቅት እንደገለፁት በሰበአዊ መብት ተሟጋች ስም የተቋቋሙት ድርጅቶች እራሳቸዉን ሊያጤኑ እና አሰራራቸዉን ሊፈትሹ ይገባል ብለዋል ፡፡

ለሰበአዊ መብት የተሰጠዉ ትርጓሜም መሰረቱ ከሆነዉ ግንድ ተለይቷል ነዉ ያሉት፡፡

በመሆኑ የሰበአዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚሉት ተቋማት ለተቋቋሙበት አላማ ሳይሆን ለፖለቲካ ማሳለጫነት እየተጠቀሙት ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጎረቤት ሃገራት አንድም ዉስጣዊ ሰላም እያጡበት ያለዉ በእንዲህ አይነት አሰራር ምክንያት ነዉ ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒሲትሩ የኛም ሃገር የሰበአዊ መብት ተሟጓች ነኝ የሚሉት ተቋማት ለህዝብ ያመጡት ፋይዳ ሳይኖር ፤ በየሚዲያዉ የሚደረግ ዘመቻ ሊቆም ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በልዑል ወሌዴ

ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply