የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በኢትዮጵያ ስራቸውን መስራት አልቻሉም-ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጥምረት 

ማክሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተባብሶ የቀጠለውን በሲቪክ ተቋማት እና ገለልተኛ የአገር ውስጥ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ላይ የሚደርስ ጫና እንዲያቆሙ ዓለም አቀፍ ጥምረት ጠይቋል።

አምስት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዳሳሰቡት በአካላዊ እና ዲጂታል ክትትል፣ የቃል ትንኮሳ፣ ማስፈራራት እና አስደንጋጭ ምልክት መላክ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ስራቸውን እንዳይሰሩ መከላከል በአገሪቱ ተፍስፍቷል።

“ከቅርብ ወራት ወዲህ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ)ን ጨምሮ በአገሪቱ ውስጥ ባሉ ታዋቂ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ላይ የኢትዮጵያ የደህንነት እና የስለላ ኃይሎች ወከባ እና ማስፈራሪያ ጨምረዋል” ሲሉም ድርጅቶቹ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሚዲያ ባለሙያዎች ስብስብ የሆነው የኢትዮጵያ ፕሬስ ነፃነት ተሟጋቾች ጥምረት በቅርቡ እንዳስታወቀው ከፈረንጆች 2019 ጀምሮ ብቻ 200 የሚደርሱ ጋዜጠኞች የታሰሩ ሲሆን

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ገለልተኛ ምርመራን እና ትችትን ለማፈን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መሰረታዊ መብቶችን በግልፅ በመጣስ ከፍተኛ እርምጃ ሄደዋል ሲሉ ድርጅቶቹ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በቀልን ሳይፈሩ ሥራቸውን ማከናወን እንዲችሉ መደረግ አለበት ሲሉም አሳስበዋል።

የዓለም ጸረ ሰብዓዊ ስቃይ ድርጅት፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ፌዴሬሽን፣ ሂዩማን ራይትስ ዋች፣ ፍሮንት ላይን ዲፌንደርስ እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባሉት ድርጅቶች በጋራ እንደገለጹት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የተጣለባቸውን የሰብዓዊ መብት ግዴታዎች፣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትን፣ የአፍሪካ የሰብዓዊና ሕዝቦች መብቶች ቻርተርን፣ የስቃይ እና ሌሎች የጭካኔ፣ ኢሰብዓዊ ወይም አዋራጅ ኮንቬንሽንን፣ የሲቪል እና የፖለቲካ ዓለም አቀፍ የመብት ቃል ኪዳንን እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን የማክበር፣ የመጠበቅ እና የማስከበር ግዴታ አለባቸው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply