የሰብዓዊ መብት አከባበር ላይ የነበረውን ችግር ለመቅረፍ በህግ ማዕቀፎች ላይ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲ…

የሰብዓዊ መብት አከባበር ላይ የነበረውን ችግር ለመቅረፍ በህግ ማዕቀፎች ላይ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰብዓዊ መብት አከባበር ላይ የነበረውን ችግር ለመቅረፍ በሕግ ማእቀፎች ላይ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብር ጽሕፈት ቤት ገለጸ:: በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይበቃል ግዛው በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የሰብዓዊ መብት የሕግ ማዕቀፎችን ለማሻሻል ረቂቅ ሰነድ ተዘጋጅቷል። ሰነዱ በክልሎች የሚታዩ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን በአግባቡ የሚለይ ነው::የድርጊት መርሐ ግብሩ ሦስተኛው ሲሆን ከዚህ በፊት ከነበሩት የተሻለ ለማድረግ እየተሰራ ነው። ከለውጡ በፊት የነበሩት የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ሰፊ ፈተና የነበረባቸው ናቸው ያሉት አቶ ይበቃል ፣ አንደኛውና ሁለተኛው የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብሮች አፈጻጸም በነበረው ፖለቲካዊ ዓውድ አመርቂ አልነበረም ብለዋል ። የአፈፃፀም ውስንነቶች እንደነበሩበትም አስታውቀዋል። ከለውጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ሦስተኛው ረቂቅ ሰነድ ብዙ ማሻሻያዎችን መያዙን ያመለከቱት ኃላፊው ፣ ለውጡ ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር ምቹ ሁኔታ የፈጠረ በመሆኑ የረቂቅ ሰነዱ ይዘት በለውጡ ዓውድ የተቃኘ ነው ብለዋል። እንደ አቶ ይበቃል ገለጻ፤ ከሕግ አንፃር ሰብዓዊ መብቶችን ይበልጥ ለማስከበር እንዲያስችሉ አዳዲስ የህግ ማዕቀፎች ይወጣሉ::መንግስት በዓለም አቀፍ ግዴታዎች ውስጥ ሊፈጽማቸው የሚችል ኃላፊነቶች ይኖሩታል። በፖለቲካዊና የሲቪል መብቶች፣ በሴቶችና ህጻናት፣ በአረጋውያን መብቶች ላይ አዳዲስ የአሰራር ሥርዓቶች ይዘረጋሉ ስለመባሉ የኢፕድ ዘገባ አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply