የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ባለፉት 10 ወራት “እጅግ አሳሳቢ” እየሆኑ መምጣታቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባለፉት 10 ወራት ባከናወናቸው የክትትል እና ምርመራ ስራ የተስተዋሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች “እጅግ አሳሳቢ እየሆኑ” መምጣታቸውን አስታወቀ። ከእነዚህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ውስጥ በመንግስት የጸጥታ አባሎች ከፍርድ ውጭ የተፈጸሙ ግድያዎች (extra-judicial killing) እና ከመጠን ያለፉ የኃይል አጠቃቀም (excessive use of lethal weapons) እንደሚገኙባቸው ኮሚሽኑ ገልጿል።

ኢሰመኮ ይህን ያስታወቀው የ10 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 3፤ 2014 ባቀረበበት ወቅት ነው። ኮሚሽኑ “እጅግ አሳሳቢ” ያላቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን የዘረዘረው የፓርላማውን “ልዩ ትኩረት የሚሹ” ጉዳዮች በሚል ባቀረበው የሪፖርቱ ክፍል ነው። 

ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጭ የሚፈጸም የዘፈቀደ እስር፣ የተራዘመ የቅድመ-ክስ እስር እና በአንዳንድ ቦታዎች የሚታይ የልጆች ሕገ ወጥ እስር ባለፉት 10 ወራት መስተዋሉን የገለጸው ኮሚሽኑ፤ በጋዜጠኞች፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እና የማህበረሰብ አንቂዎች ላይ ያነጣጠረ እስር እና አስገድዶ መሰወር (enforced disappearance) መፈጸሙንም አስታውቋል። በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተደነገገበት ወቅት “የሰብአዊ መብት መርሆችን ያልተከተለና በብሔር ማንነት ላይ ያነጣጠረ የተስፋፋ እስር ተፈጽሞ” እንደነበርም ጠቅሷል። (በተስፋለም ወልደየስ – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

The post የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ባለፉት 10 ወራት “እጅግ አሳሳቢ” እየሆኑ መምጣታቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ appeared first on Ethiopia Insider.

Source: Link to the Post

Leave a Reply