የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 12 ተሽከርካሪዎች በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ ጉዞ መጀመራቸው ተገለጸ

አርብ ኀዳር 9 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የአለም የምግብ ፕሮግራም የሰብአዊ እርዳታ የጫኑ 12 ተሽከርካሪዎች በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ ክልል ጉዞ መጀመራቸው ተገልጿል፡፡

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በአፋር ክልል በኩል ለትግራይ ክልል ህዝብ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም መሠረትም ኹለት የነዳጅ ቦቴዎችን ጨምሮ የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ 12 ተሽከርካሪዎች ዛሬ በአፋር ኮሪደር በኩል ወደ ትግራይ ክልል ጉዞ መጀመራቸው የአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

የአፋር ሕዝብና መንግስት ለወንድም የትግራይ ሕዝብ የሰብዓዊ እርዳታው እንዲደርስ ካሁን በፊት ሲያደርገው እንደነበረው ኹሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራም ገልጿል።

The post የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 12 ተሽከርካሪዎች በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ ጉዞ መጀመራቸው ተገለጸ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply