የሰንበት መረጃዎች (አሻራ ታህሳስ 25፣ 2013ዓ.ም) 1) ኢዜማ ከ 95 ሺ  በላይ ኮንዶሚኒየም እና 200 ሺ  ካሬ ሜትር ቦታ በአምስት ክፍለከተሞች ብቻ  በአዲስ አበባ እንደተዘረፈ ሰኔ…

የሰንበት መረጃዎች (አሻራ ታህሳስ 25፣ 2013ዓ.ም) 1) ኢዜማ ከ 95 ሺ በላይ ኮንዶሚኒየም እና 200 ሺ ካሬ ሜትር ቦታ በአምስት ክፍለከተሞች ብቻ በአዲስ አበባ እንደተዘረፈ ሰኔ…

የሰንበት መረጃዎች (አሻራ ታህሳስ 25፣ 2013ዓ.ም) 1) ኢዜማ ከ 95 ሺ በላይ ኮንዶሚኒየም እና 200 ሺ ካሬ ሜትር ቦታ በአምስት ክፍለከተሞች ብቻ በአዲስ አበባ እንደተዘረፈ ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም ይፋ አድርጎ ነበር፡፡ በሁሉም ክፍለከተሞች የተዘረፈው ቤት እና ንብረት ሲሰላ ኢዜማ ከደረሰበት ከፍ እንደሚልም ተገምቷል፡፡ ዕጣ የወጣላቸው ኮንዶሚኒየሞች ሁሉ በጃዋር መሪነት በኦሮሚያ ብልፅግና አስተባባሪነት ለወጣቶች ተሰጥተዋል፡፡ ታዲያ ኢዜማ ይሄን ጥናቱን የህዝብ ተወካዮች እና ሚዲያዎች ባሉበት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድርም ባለበት እንደገና መፍትሄ ፈላጊ ውይይት ሊያደርግ ነበር፡፡ ከተማ አስተዳድሩ ግን ስለ አዲስ አበባ መሬት ወረራ ውይይትም ሆነ መግለጫ አትሰጥም ብሎ ከከለከለው ስድስተኛ ወሩን አስቆጥሯል፡፡ ኢዜማም ክስ የ…ጀመረ ሲሆን የክሱ ብይን ነገ ሰኞ በቀን 26 ይፋ እንደሚሆን እጠብቃለሁ ሲል መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የለውጡ የሚባለው መንግስት ውይይት እና መግለጫ መስጠትን እንኳን የሚከለክል ፍፁም አምገነናዊ መሆኑን እያሳየ ነው፡፡ ከሰሞኑ እንኳን ኢዴፓ መግለጫ አትሰጥም ተብሎ ተከልክሏል፡፡ ባልደራስም በተደጋጋሚ ሲከለከል የቆየ ሲሆን ለመንግስት ቅርብ ነው የሚባለው ኢዜማም ውይይት እንኳን እንደተከለከለ ተሰምቷል፡፡ 2) ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት እና አቶ ልደቱ አያሌው ፓርቲያቸው በመሰረዙ ምክንያት አዲስ ፓርቲ ሊመሰርቱ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ ፓርቲው ሀገራዊ ወይም ዜግነት ተኮር ፓርቲ ሲሆን የአፋር፣ የደቡብ እና የሌሎች አካባቢ ፓርቲዎችም አዲስ ከሚመሰረተው ፓርቲ ጋር ለመጣመር ከወዲሁ ፍላጎት እንዳሳዮ ተሰምቷል፡፡ ነገር ግን የፓርቲውን ምስረታ አስመልክቶ መግለጫ ሊሰጡ የነበሩት እነ አቶ ልደቱ መግለጫ እንዳይሰጡ በመንግስት ተከልክለዋል፡፡ በዚህ አካሂድ ቀጣዮ ምርጫ ምን አይነት ቅርፅ ሊኖረው እንደሚችል ግልፅ ነው፡፡ 3) የአማራ ብልፅግና ለሶስት ቀናት ባደረገው ሀገራዊ ሁኔታን የመገምገም ሂደት የተረኝነት ዝንባሌ አለ በሚለው የጋራ መግባባት ደርሷል፡፡ አቶ አገኘሁ ተሻገር ሲያጠቃልሉ የተረኝነት ዝንባሌ ስላለ በጋራ ወንድማማቻዊ ትግል እናደርጋለን ያሉ ሲሆን፣ ሌሎች የፌዴራል እና የክልል አመራሮችም ጠንከር ያለ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ብልፅግና ሁሉም ብሄረሰቦች በአማራ ጠላትነት እንዲቆሙ የሚሰራ ፀረ ህዝብ ድርጅት መሆኑም በይፋ ተገምግሟል፡፡ ተረኛ ነን የሚሉ ብልፅግናዎች የአማራ ባለሀብቶችን በተዛባው የፍትህ ስራዓታቸው እያሳቀቁ፣ አንዳንዶች ገንዘብ አምጡ እያሉ፣ በፋይናንስ ደህነቶች እያንገራገሩ በምቾት እንዳይሰሩ እያደረጓቸው እንደሆነም ተገምግሟል፡፡ እንደ አሻራ መረዳት ልክ ህወኃት ለእነ አቦይ ስብሃት፣ አባይ ፅሃየ የማይታይ ትልቅ መንግስታዊ ስልጣን የሰጠውን ያህል ብልፅግናም ኢኮኖሚውን ለአምባሳደር ግርማ ብሩ፣ የሀገሪቱን ደህነት ለአባዱላ ገመዳ፣ የውጭ ግንኙነት እና ፖለቲካውን ለሌንጮ ባቲ፣ ፕሮፖጋንዳው ለነታየ ደንዳዓ ስልጣኑን አጠራቅሞ የሰጠ ሲሆን የደቡብ መፈራረስ፣ የከንሶ እና የመተከል እልቂት፣ የአዲስ አበባ መዘረፍ ፣ የንግድ ባንክ መሽመድመድ ከዚህ እዝ በሚመነጭ የተረኝነት መንፈስ እንደሆነ አሻራ ግምት ወስዷል፡፡ እንደ ቡና፣ አብሲኒያ እና የመሳሰሉትን ባንኮች ለማኮሰስ የምርመራ ስራ የተጀመረ ሲሆን ታላቅ ውስጣዊ ቅሬታም ፈጥሯል፡፡ የንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት የነበረው አቶ በቃሉ ዘለቀ በተረኝነት በባጫ ጊና ተተካ፡፡ ንግድ ባንክም መንገዳገድ ገጠመው፡፡ አቶ በቃሉ ወደ አብሲኒያ ተዛውረው አብሲኒያን ማሳደጋቸው የተረኞችን ዓይን ያቀላ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ 4) ከመተከል የተፈናቀሉ ዜጎች 140 ሺ አካባቢ የደረሱ ሲሆን አስቸኳይ የህክምና እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው በቦታው የሚገኘው ዘጋቢችን አረጋግጧል፡፡ ከፍተኛ የመድሃኒት እጥረት ያለ ሲሆን፣ እርዳታው ለመስጠት በተለያየ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ወገኖች አሉ፡፡ በፌዴራል መንግስት ሆኖ በደቡብ ተወላጆች ብቻ እንዲመራ የተወሰነው የመተከል ጉዳይ የተወሰነ መረጋጋት ታይቶበታል፡፡ ኮማንድ ፖስቱን መንግስታዊዉን አቶ ተስፋየ ቤልጂጌ ሲመሩት ወታደራዊዉን ብርጋዴር ጀኔራል አስራት ደሬፎ ይመሩታል፡፡ በደቡብ ተወላጆች ብቻ እንዲመራ የተወሰነው የአማራ እና የኦሮሞ ብልፅግናዎች መተማመን ባለመድረሳቸው እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ ባለፈው የመተከልን ህዝብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲያወያዮ የአማራ ቴሌቪዥንን ትተው የኦሮሚያን መውሰዳቸው ሲያስተቻቸው የነበረ ሲሆን፣ የአማራ ብልፅግና አመራሮችን በቢሻንጉል አመራሮች እንዲሰደቡም አድርገዋል፡፡ የመተከል ዞን አስተዳዳሪ (ከሰሞኑ የታሰረው) አቶ አትንኩት ሽቱ የአማራ አመራሮችን ወርፎ ነበር፡፡ ሰልጥነው የገቡ ተናጋሪ ሽማግሌዎችም የአማራ አመራር ጁንታ ነው፡፡ አብይ አህመድ የመቀሌውን ጁንታ ሲያጠፋ የአማራ አመራር እና ፋኖ መተከል መጥቶ ቤት ያቃጥላል፡፡ ይዘርፋል፡፡ ጉምዝ ሱዳናዊ ነው ይላል ብለው የውሸት ወቀሳ አቅርበዋል፡፡ ይሄን ሁሉ የተመለከቱ ሰዎች አብይ አህመድን የተረኝነት እና የስልጣን ብሄርተኛ አድርገው እየፈረጇቸው ነው፡፡ 5) ኢትዮጵያ በቅርብ የኮሮና ክትባት ስትጀምር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሃያ ከመቶ ዜጋዋ ተደራሽ እንደምታደርግ ተገልጻል፡፡ በዚህም አረጋውያን፣ የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች ተጋላጭ ዜጎች ቅድሚያ ክትባቱን ይወስዳሉ፡፡ ለክትባቱ አስፈላጊ ግባት ሁሉ እየተሟላ እንደሆነ ጤና ሚኒስትር ገልፃል፡፡ 6) የአልነጃሽ መስጊድ መጎዳት ቁጣ የቀሰቀሰ ሲሆን የተቃውሞ ሰልፍ እየተጠራም ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል ወታደሩን ጨምሮ ንፅሃን ዜጎች እያለቁ ለመስጊዱ ብቻ መቆርቆር ሚዛናዊ አይደለም፡፡ ፖለቲካዊ ነው እያሉ ነው፡፡ መስጊዱን ህወኃት ይጉዳው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አልታወቀም፡፡ የህወኃት አመራሮች ጦር እና ስንቅ፣ ራሳቸውንም ጨምሮ በመስጊድ እና በአብያተክርሲቲያናት መደበቃቸው የጉዳቱ መንስኤ ሳይሆን እንደማይቀር መላምት እየወጣ ነው፡፡ የጦርነት አንዱ አውዳሚ ገፅታው ተደርጎም ተወስዷል፡፡ 7) በገና ላሊበላ፣ በጥምቀት ጎንደር፣ ከጥር 10 እስከ 30 ደግሞ ባህርዳርን ልዮ የጀልባ ትርዕይት ተጠባቂ ሁነታዊ ዝግጅቶች ሆነዋል፡፡ ብሩህ ቀን https://m.youtube.com/channel/UCsfBw4xrhJzdMTzhWk_uX2A…

Source: Link to the Post

Leave a Reply