የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት በሚዲያዉ ዘርፍ ወደ ኢትዮጵያ ብቅ ማለቱ ከፍተኛ ስጋት ይኖረዋል ተባለ፡፡በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ የመጀመሪያዉ ነዉ የተባለለትን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አሚኮ…

የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት በሚዲያዉ ዘርፍ ወደ ኢትዮጵያ ብቅ ማለቱ ከፍተኛ ስጋት ይኖረዋል ተባለ፡፡

በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ የመጀመሪያዉ ነዉ የተባለለትን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አሚኮ በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ወይንም ሰዉ ሰራሽ እስተዉሎት አማካኝነት ዜናዎችን ማቅረብ መጀመሩን ተከትሎ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረዉ ባለሙያዎች አንስተዋል፡፡

የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ መዋል በማኅበረሰቡ ውስጥ ስለሚኖረው ሚና ተጨባጭ መረጃዎችን በማቅረብ ጉዳቱ እና ጥቅሙን በማንሳት በአለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ክርክር እየተደረገበት ይገኛል።

ይህ ቴክኖሎጂ በሚዲያዉ ዘርፍ እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ ስጋትም ተስፋም እንዳለዉ ባለሙያዎች ሃሳባቸዉን በስፋት ይሰነዝራሉ፡፡

በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ የመጀመሪያዉ ነዉ የተባለለትን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አሚኮ በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ወይንም ሰዉ ሰራሽ እስተዉሎት አማካኝነት ዜናዎችን ማቅረብ መጀመሩን በቅርቡ አስታወቋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ የሰው ሠራሽ አስታውሎት መረጃን መጀመሩን ተከትሎም መነጋጋሪያ ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

እኛም ለመሆኑ አሚኮ በዚህ ጊዜ ቴክኖሎጂዉን ለምን መጠቀም ፈለገ፤ የሚኖረዉ ጠቀሜታና በጋዜጠኝነት ኢንዱስትሪ ላይ የሚያስከትለዉ ተጽዕኖስ እንዴት ይታይል? ስንል ጠይቀናል፡፡

በአማራ ሚዲያ ኮረፖሬሽን የሰልጥናና ምርምር ዳየሬክተሩ አቶ ሃሰን መሃመድ ተቋማቸዉ ስለምን የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎትን መጠቀም ጀመረ ብለን ላነሳንላቸዉ ጥያቄ ቴክኖሊጂዉ ብዙ ጠቀሜታ ስላለዉና የጋዜጠኞችን ደህንነት ለማስጠበቅ እንዲሁም ለ ህብተረተሰቡ አማራጭ ይዞ ለመምጣት ባመሰብ እንደሆነ ነግረዉናል፡፡

የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ተፅእኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ስለመምጣቱ የዘርፉ ተማራማሪዎች ጭምር ያስረዳሉ፡፡ ዘርፉ በቅጡ ቁጥጥር ካልተበጀለትም የሰዉን ልጅ አደጋ ላይ እንደሚጥል ተመራማሪዎቹ አስጠንቅቀዋል፡፡

በርግጥ በሌሎች ዘርፎች ላይ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት በስፋት ቢታይም በኢትዮጵያ ሚዲያ ዘርፍ ብቅ ማለቱ ለሙያዉ የራሱ በጎ አስተዋዕፅኦ እንዳለዉ አቶ ሃሰን ይናገራሉ፡፡

ይህን የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት በሚዲያዉ ዘርፍ መጠቀም ቴክኖሎጂን ከማስፋፋት አኳያ በጎ የሚባለ ጠቀሜታ ቢኖረዉም ፤ ይሑን እንጅ የጋዜጠኛዉን ስራ በመሻማት የስራ አጥነት ቁጥሩን ይጨምረዋል የሚል አከራካሪ ሃሳብም ይነሳል፡፡

ለመሆኑ ይሕን ጉዳይ የአማራ ሚዲያ ኮረፖሬሽን አሚኮ እንዴት አይቶት ይሆን ብለን ላነሳነዉ ጥያቄ አቶ ሃሰን አሚኮ ጋዜጠኞችን በቴክኖሎጂዉ ሙሉ በሙሉ የመተካት ፍላጎት ስለሌዉ ባለሙያዎችን መቅጠሩን አያቆምም ብለዋል፡፡

ተቋሙ ይህን ምላሽ ቢሰጥም ከጋዜጠኝነት ሙያ አንፃር ይህ ቴክኖሎጂ እንዴት ይታያል ስንል ባባህር ዳር ዩንቨርሲቲ የጋዜጠኝነ ትና ስነ ተግባቦት መመህር አቶ ሰለሞን ሙሉን ጠየቅን፡፡

እርሳቸዉ ቴክኖሎጂዉን መጠቀሙ ይዟቸዉ የሚመጣዉ በጎ እድሎች ቢኖሩም ነገር ግን በእኛ ሀገር ተጨባጭ ሁኔታ ሚዲያዉ ታማኚነቱን ሊያጣ ይችላል ይላሉ፡፡

የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት በኢትዮጵያ በሚዲያዉ ዘርፍ መጀመር የጋዜጠኞችን ደህንነት ለማስጠበቅ ነዉ ተብሎ በተነሳዉ ሃሳብ ላይ ግን መመህር ሰለሞን ይህ መፍትሄ ሊሆን አይችልም ብለዋል፡፡

ሌላዉ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ቴክኖሎጂ የጋዜጠኞችን ቦታ ሸፍኖ መስራቱ ሁለት ትላልቅ አሉታዊ ተጽዕኖችን እንደሚያስተከትል ይነሳል፡፡

አንደኛዉ ሰዉኛ ባህሪን ማጣትና የስራ አጥ ቁጥርን መጋፋት እንደሆነ አቶ ሰለሞን አስንተዋል፡፡
እናም ነበራዊ ሁኔታዎችን አይቶ መጠቀም እንደሚገባም መምህሩ አሳስበዋል፡፡

የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ተማራመሪዎች በበኩላቸዉ ቴክኖሊጂዉ ገደብ ካልተበጀለት ሐሰተኛ ወሬዎች የሚዛመቱበት ፍጥነት እና ብዛት ሊመጨመር እንደሚችል በመግለጽ ይህም የሕዝብ አመኔታን በማሳጣት እኩልነትን ያርቃል የሚል ስጋት እንዳላቸዉ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ አንስተዋል።

በአባቱ መረቀ
ህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply