የሰው ልጅ በህይወትም በሞትም ክብሩን ለምን ይጣ – አሳሩ በዛብህ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለፈው ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል፣መተከል ዞን፣ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ በግፍ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 207 መድረሱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በዚሁ ሪፖርት ላይ አስክሬን የመፈለጉና የቀብር ስነ-ስርዓት አፈፃፀሙ ሰብዓዊ በሆነ መልኩ እንዲከውን ጥሪ አቅርቧል፡፡አሳሩ በዛብህም ይህ ሳይከነክነው አልቀረም፡፡ ንፁሃን በህይወት ለመኖር ደህንነታቸውን የሚያስጠብቅላቸው ባይኖር እንኳን ግብዓተ መሬታቸው ምናለ በስርዓቱ ቢፈፀም ሲል በማማረር ላይ ነው፡፡

ምሬትና ትዝብቱን፤ ጭንቀትና ብሶቱን ለወዳጁ ምክረሰናይ መፍትሔ በመሻት በሳምንታዊው ደብዳቤው ከትቦ ልኮለታል፡፡

ምክረ ሰናይም ለአሳሩ በዛብህ ደብዳቤ ምላሹን ይሰጣል

ትዕግስቱ በቀለ እንደ አሳሩ በዛብህ

ዩሃንስ አሰፋ እንደ ምክረሰናይ ያቀርቤታል፡፡

አዘጋጅ፡ ዩሃንስ አሰፋ

ቀን 20/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply