የሰዎች ስብዕና ከአንድ በላይ በሆኑ ክፍሎች የተዋቀረ መሆኑ በታዋቂው ሲግመንድ ፍሩድ የስነ-ልቦና ጽንሰ-ሀሳብ መሠረት ይገለጻል፡፡ #እነዚህም ሶስቱ የስነ ልቦና መዋቅሮች• ኢድ (id)፣ •…

የሰዎች ስብዕና ከአንድ በላይ በሆኑ ክፍሎች የተዋቀረ መሆኑ በታዋቂው ሲግመንድ ፍሩድ የስነ-ልቦና ጽንሰ-ሀሳብ መሠረት ይገለጻል፡፡

#እነዚህም ሶስቱ የስነ ልቦና መዋቅሮች
• ኢድ (id)፣
• ኢጎ (Ego)
• ሱፐር-ኢጎ(Superego) ተብለው ይጠራሉ፡፡

ሶስቱም የስብዕና መዋቅሮች በእያንዳንዱ ግለሰብ ላይ በተለያየ መልኩ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ መሆናቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ከሶስቱ የስብዕና አካት አንዱ ኢድ(id) ነው፡፡ ኢድ ከተወለደንበት ጊዜ ጀምሮ የነበረ ብቸኛው የስብዕናችን አካል ሲሆን፤ ይህ የስብዕና አካል በደመነፍስ የሚመራ ባህሪን አካቷል፡፡ ሁሉንም ፍላጎቶች ወዲያውኑ ለማሟላት የሚጥር ሲሆን፤ ፍላጎቶች ወዲያውኑ ካልተሟሉ የስብዕና ውጥረት ሊፈጠር እንደሚችል ይገለጻል፡፡

የመጨረሻው እና ሶስተኛው የሰዎች ስብዕና አካል ሱፐር-ኢጎ (Superego) ወይም ህገ ልቦና( ህሊና) ሊባል የሚችል ሲሆን፤ ከወላጆችና ከማህበረሰብ የሚገኝ በውስጥ የተቀመጡ የሥነ-ምግባር መርህ እና አመለካከቶችን የሚይዝ የስብዕና ክፍል እንዲሁም ውሳኔና መመሪያዎችን የሚሰጥ ይሆናል፡፡

የአእምሮ ስፔሻሊስት ሀኪም የሆኑት ዶክተር እስጢፋኖስ እንዳላማው፤ ሁለተኛው እና ከሶስቱ የስብዕና መዋቅሮች አንዱ የሆነው ኢጎ እውነታን ከግምት ውስጥ የማስገባ እና የመመዘን አቅም እንዳለው ተናግዋል፡፡

• ኢጎ ከነባረዊ ሀኔታ በመነሳት ደመነፍሳዊ ስሜት ለመቆጣጠር ይረዳል
• የውስጥ ስሜቶች እና ግፊቶች መቆጣጠር እና መመጠን
• የገሀዱ አለምን ለመረዳት እና ከሰዎች ጋር ተቻችሎ ለመኖር ያስችላል
• በኢድ እና በሱፐር ኢጎ መካከል በመግባት፤ በደመነፍስ እና በሞራል እሴት ያለውን ቅራኔ ከእውነታ አንጻር በማስረጃ እና በመረጃ መዝኖ የመዳኝነት የማስታረቅ ስራ ይሰራል።

ጤናማ ኢጎ በሰዎች ዘንድ ከዳበረ ነገሮችን የመቋቋም ችሎታ እንዲሁም ከእውነተኛ አንጻር መመዘን የሚስተዋል ይሆናል፡፡

የስብዕና ክፍል የሆነው ኢጎ ራስን ከፍ ከፍ በማድረግ ከእውነታው ወይም ከገሀዱ አለም ጋር ለመገናኘት የሚያግዘን ነው ተብሏል፡፡

ኢጎ(Ego) ከ ኢድ(id) ወይም በደመነፍስ ከሚመራ ባህሪ የሚዳብር ሲሆን፤ ኢጎ የሚሠራው በእውነተኛው መርህ ላይ በመመርኮዝ ነው ፡፡

የኢድ እና የኢጎን ጸንሰ ሃሳብ ልዩነትን በቀላሉ ለመረዳት እንደ ምሳሌ የሚጠቀሰውን ለማስሳት ያህል፤ አንድ ረዘም ያለ ስብሰባ ላይ ተቀምጠው ቆይተዋል፡፡ ስብሰባው በመቆየቱ እርሶ የርሃብ ስሜት ተሰምቶታል፡፡

ታዲያ በዚህ ጊዜ ኢድ(id) ስብሰባውን አቋርጠው እንዲወጡ እና ምግብ እንዲመገቡ ይገፋፋዎታል ፤ ኢጎ(Ego) ደግሞ በተራው ረዘም ያለ ጊዜን የወሰደው ስብሰባው እስኪጠናቀቅ ድረስ በትግስት ተረጋግተው እንዲቀመጡ በተቃራኒው የሚገፋፋዎት ይሆናል፡፡ ኢጎ ደመነፍሳዊ እና ስሜቶች የመመጠን እንዲሁም የመቆጣጠር አቅም እንዳለው ባለሞያው ነግረውናል፡፡

በህብረተሰቡ ዘንድ ሁለተኛ እና ደመነፍሳዊን ከእውነተኛው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚዳኘው የስብዓና ባህሪ መዋቅር የሆነው ኢጎን፤ እንደ መጥፎ ባህሪ እና እክል የሚወሰድበት ሁኔታ ስህተት መሆኑም ይነገራል፡፡

ኢጎ ስህተት የሚሆነው ሚዛኑን ሳይጠብቅ ሲቀር እና የእኔነት ባህሪ ከቁጥጥር ውጭ ሲሆን እንዲሁም አንዳንድ የስነ ልቦና እክሎች እንደ ናርሲስቲክ ባህር ወይም አፍቅሮተ እራስ የሚኖር ከሆነ እና የኢጎ ስራ በትክከለኛ መልኩ ሳይዳብር ሲቀር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

• ግላዊ ፍላጎቶችን፤ ማህበረሰባዊ እና ሞራላዊ ቅራኔን በማያስከትል መልኩ ማራመድ መቻል

• ውስጣችንን ምቾት የሚነሱ ጉዳዮች ሲያጋጥሙን በቀልድ አዋዝተን ለማለፍ መሞከር

• ራስን ከጭንቀት ማራቅ፣ ከራስ በላይ ለሌሎች መልካም ነገርን ማድረግ ልጁን በህመም ያጣ ወላጅ የሚፈጠርበትን የቁጭት ስሜት ለማስታገስ: በጎ አድራጎት ማህበር አቋቁሞ ሰዎችን ማገዝ እንደ ምሳሌ የሚጠቀስ ነው፡፡

• የስነልቦና ዝግጅት በማድረግ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላል ነገር ግን ከተከሰቱም በዝግጅቱ ለመቋቋም መቻል ጥሩ ኢጎ ያለው ወይም በተረጋጉ እና በነገሮች በቀላሉ በማይረበሹ ሰዎች የሚዘወተሩ እና ከጭንቀት መከላከያ መንገዶች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply