የሱማሊያ የበረራ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኳታር አየር መንገድ ቅዳሜ’ለት በሱማሊያ አየር ክልል ላይ ለጥቂት ከመላተም ተርፈዋል ተብሎ የተሠራጨውን መረጃ አስተባብሏል…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/Scu_TUrnY_OoZ7-FwysDE1zph2ShAkkQvDgt8ZbWpVZvqyMqyDuE6wCjaUCaY-ja7bK0MrnoQAfgnSEeEGYBTqlaf17chS7SnS6TCCu9oRE_oPYTzF5GjZlvxpm60IaFroaevB0ifknoMz13G_IRZb8srMRmPrIEfhqqMdmHBJhXeXN9MyqBh4prSPK0NWJH7Zhdhuepn-4D6YFe_vywV1n4KjDtkrIC1Gj04Ab4oDW3ZKYmZ5qgbvJJltvMUE2idFj8XZGUwB9Xcoi-nW0W4-jpuPxiTXhgSLvauaLg2N78HwliaUPj5J1Q2hMs0PLZmSpL-LeDDGZWNpWZEoTrtQ.jpg

የሱማሊያ የበረራ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኳታር አየር መንገድ ቅዳሜ’ለት በሱማሊያ አየር ክልል ላይ ለጥቂት ከመላተም ተርፈዋል ተብሎ የተሠራጨውን መረጃ አስተባብሏል።

ባለሥልጣኑ፣ ኹለቱ አውሮፕላኖች አስተማማኝ የከፍታ ልዩነት ነበራቸው ብሏል።

በሱማሊያ በረራ ተቆጣጣሪዎች የተሳሳተ መመሪያ ምክንያት ሊጋጩ ነበር የተባሉት የመንገደኞች አውሮፕላኖች፣ ከዶሃ ወደ ኡጋንዳ ሲበር የነበረው የኳታሩ አውሮፕላንና ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ ሲበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ናቸው።

አደጋው ሊከሰት የነበረው፣ የኢትዮጵያው አውሮፕላን በ39 ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ እየበረረ ሳለ፣ የበረራ ተቆጣጣሪዎች በተመሳሳይ መስመር ላይ በ38 ሺህ ጫማ ይበር የነበረው የኳታር አውሮፕላን ከፍታውን ወደ 40 ሺህ ጫማ ከፍ እንዲያደርግ መመሪያ በመስጠታቸው ነው ተብሏል።

አውሮፕላኖች ከመላተም የተረፉት፣ በተገጠመላቸው የማስጠንቀቂያ ሥርዓታት እገዛ እንደኾነ ተገልጧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply