
ሱዳን ላለፉት ቀናት በግጭት እየታመሰች ነው።የአገሪቱ ጦር አዛዥ ጀነራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሽ ልዩ ኃይል አዛዥ ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ አንጃ ፈጥረው ለስልጣን ሽሚያ ውጊያ ውስጥ ገብተዋል። የበርካቶችን ህይወት የቀጠፈው ይህ ግጭት የሱዳንን እጣ ፈንታንም ጥያቄ ውስጥ ከትቶታል። ስጋቱ ግን ለሱዳናውያን ብቻ አይደለም። በሱዳን ያለው ሁኔታ ተባብሶ ከቀጠለ መዘዙ ለምስራቅ አፍሪካም የሚተርፍ መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።
Source: Link to the Post