የሱዳን ባለስልጣናት በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር መካከል ያለውን ግጭት ተከትሎ ውንጀላቸውን መቀጠላቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያና ሱዳን በአዋሳኝ ድንብሮች መካከል ያለውን ግጭት ለመፍታት እንደተስማሙ ቢነገርም የሱዳን ባለስልጣናት ግን ኢትዮጵያን እየወነጀሉ ነው፡፡የሱዳን የመረጃ ሚኒስትር ፋይሰል ሞሀመድ ሳላህ ባለፉት ቀናት ግዛታችንን ተሻግሮ በተሠነዘረው ጥቃት የኢትዮጵያ ጦር ከሚሊሻዎች ጀርባ በመሆን ድጋፍ ሰጥቷል ሲሉ ከሰዋል፡፡ሚኒስትሩ የሀገራቸውን የደህንነትና የስለላ ሪፖርት ዋቢ አድርገው እንደተናገሩት የተቃጣባቸው ጥቃትና መሳሪያዎቹም የኢትዮጵያ ጦር እንደሆኑ ተረጋግጧል፡፡

ምንም እንኳን ሱዳን ይህን ክስ ታቅርብ እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት ክሱን ቀደም ሲል ማጣጣሉ አይዘነጋም፡፡ሚኒስትሩ ከወቀሳው ባለፈ የሱዳን መንግስት ማንኛውንም የወዳጅነትና ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔዎችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡በተያያዘ የሱዳን ጦር ተጨማሪ ሰራዊቱን በአዋሳኝ ስፍራ በዋድ አሮውድ ላይ ማስፈሩን የሀገሪቱን የዜና ምንጮች ዋቢ አድርጎ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ሚሊሻዎችም ተጨማሪ ሰራዊትና የጦር መሣሪያዎችን በአብድ አል- ራፊያ አካባቢ ማስፈሯ ቢዘገብም ከኢትዮጵያ በኩል አስከ አሁን የተሰጠ ምላሽ ግን የለም።

***************************************************************************

ዘጋቢ፡ ዩሐንስ አሰፋ

ቀን 19/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply