የሱዳን ባለስልጣናት ኢትዮጵያውያን ሴት ተኳሾችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸዉ ተሰምቷል፡፡

በሱዳን እየተካሄደ ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ ከኢትዮጵያ አዋሳኝ ገደሪፍ ግዛት ባለስልጣናት ለፈጥኖ ደራሹ ሃይል ተኳሾች ሆነው በማገልገል ላይ የነበሩ ያላቸዉን 6 ኢትዮጵያውያን ሴቶችን በቁጥጥር ስር አዉለዋል፡፡

ይህ ክስተትም የሱዳን ጦር የውጭ ዜጎችን በቅጥረኝነት ይመለምላል የሚለውን አባባል የበለጠ ያረጋግጣል ተብሏል፡፡

ምንጮች ለሱዳን ትሪቡን እንዳረጋገጡት እነዚህ ሴቶች በኢትዮጵያ ያገኙትን ልዩ የመተኮስ ብቃታቸውን በመጠቀም በፈጥኖ ደራሽ ሃይል ውስጥ ከአንድ አመት በላይ ሲሰሩ ቆይተዋል።

በሱዳን ጦር ሃይሎች (SAF) እና በፀጥታ ኤጀንሲዎች ላይ በሚደረጉ ዘመቻዎች ላይ ተሳትፈዋል የተባለው በስልካቸው ላይ በተገኙ ወታደራዊ ተሳትፎ እና የጦር መሳሪያ ምስሎች ነው።

ሴቶቹ በካርቱም ጦርነቱ መባባሱን ተከትሎ በአማራ ክልል በኩል ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ነዉ የተነገረዉ፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ሲደርሱም በሰላም እንዲያልፉ እና እንዲከፈላቸው ዝግጅት ተደርጎ ነበር ተብሏል።

ከዚህ ቀደም ከፈጥኖ ደራሹ ሃይል ጋር ሲዋጉ ነበር የተባሉ የደቡብ ሱዳን ዜጎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ተከትሎ ነዉ እነዚህ ኢትዮጵያዊያንም ሊታሰሩ የቻሉት ተብሏል፡፡
@ሱዳን ትሪቡን

በእስከዳር ግርማ

ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply