You are currently viewing የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ከሰኞ ጀምሮ ለሰባት ቀናት የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማሙ – BBC News አማርኛ

የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ከሰኞ ጀምሮ ለሰባት ቀናት የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማሙ – BBC News አማርኛ

https://ichef.bbci.co.uk/news/1024/branded_amharic/1a2a/live/b7b3dbd0-f79c-11ed-92cc-b3a9bf1f67e9.jpg

በሱዳን የሚካሄደው ውጊያ ስድስተኛ ሳምንቱን በያዘበት በአሁኑ ጊዜ ተቀናቃኝ ኃይሎቹ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደረሱ።
ከዚህ ቀደም በሱዳን መደበኛ ሠራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል ተኩስ ለማቆም ተደርሰው የነበሩት ስምምነቶች ተግባራዊ ሳይሆኑ ሲጣሱ እንደነበር ይታወሳል። የአሁኑ ስምምነት ግን በተለየ ሁኔታ ተፈጻሚነቱን ለመቆጣጠር የሚያስችል አካል እንዳለው አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ ስምምነቱን በማስመልከት ያወጡት መግለጫ አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply