የሱዳን እና የህወሓት ወታደሮች በረከት በተባለ አካባቢ ዝርፊያ ፈጽመዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሀምሌ 7/2014 የሱዳን…

የሱዳን እና የህወሓት ወታደሮች በረከት በተባለ አካባቢ ዝርፊያ ፈጽመዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሀምሌ 7/2014 የሱዳን እና የህወሓት ታጣቂዎች በኢትዮ ሱዳን አቅራቢያ በረከት በሚባለው አካባቢ ልዩ ስሙ መቻታ እና ዋልድ በሚባሉ ቦታዎች ላይ በ12 ፓትሮል ድሽቃ በመተኮስ በርካታ የእርሻ ልማቶችን አውድመዋል። በዚህም በኢትዮጵያ ለግብርና (ለትራክተር) ስራ ሊውል የነበረ 8 በርሜል ነዳጅ፣ ለጉልበት ሰራተኞች የተዘጋጀ 60 ኩንታል እህል ዘርፈው ወስደዋል። ይህ ከሆነ በኋላ መከላከያ ሠራዊት ወደ አካባቢው ቢያቀናም ፊት ለፊት ሊገኙ አልቻሉም። ከዚሁ ጥቃት ጋር እጃቸው አለበት የተባሉ ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው። ሸገር ፕሬስ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply