የሱዳን እና የኢትዮጵያ አርስ በእርሳቸው መካሰሳቸውን መቀጠላቸው ተገለጸ

ሱዳን የእርሻ መሬታችንን ከኢትዮጵያ ነጥቀን የግላችን አድርገናል ስትል ኢትዮጵያ በበኩሏ የእርሻ መሬታችንን ባልተገባ መልኩ ሱዳን ወራብናለች ብላለች፡፡የሱዳን መንግስት ከዚህ ቀደም ባልተገባ እና ህጋዊ መነሻ በሌለው መልኩ ኢትዮጵያ ተቆጣጥራው የነበረውን የእርሻ መሬታችንን በአሁኑ ሰዓት አብዛኛውን የመከላከያ ሰራዊታችን ተቆጣጥሮታል ሲል አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ከተሰማራበት ጊዜ አነስቶ በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር መካከል ውጥረቶች ነግሰው ከርመዋል ተብሏል፡፡ሱዳን አል-ፋሽቃ የተባለው የእርሻ መሬት የእኛ ሆኖ ሳለ ለረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች ሲጠቀሙበት ቆይተዋል በአሁኑ ሰዓት ግን ተቆጣጥረነዋል ስትል ገልፃለች፡፡

የሱዳን የመረጃ ሚኒስቴር ፋይሰል ሳሊ “አለመግባባት እና ችግሮችን ለመፍታት በውይይት እናምናለን፤ የመከላከያ ሰራዊታችን ግን ግዴታውን መወጣት አለበት ሁሉንም መሬታችንን በቁጥጥር ስር ማዋል አለበት በአሁኑ ሰዓትም መከላከያ ሰራዊታችን ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚሆነውን መሬታችንን ተቆጣጥሮታል” ብለዋል ሲል የዘገበው ፕሬስ ቲቪ ነው፡፡

ፕሬስ ቲቪ በዘገባው ይህንንም አስፍሯል፤ ባሳለፍነው ሳምንት ሁለቱ አገራት በጉዳዩ ላይ በነበራቸው ውይይት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን “የሱዳን ወታደር በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ፈፅሟል፤ የኢትዮጵያን የእርሻ መሬት ወሮታል፤ በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ ጥቃት ፈፅሞ ንፁኃንን ለሞት ዳርጓል እና ገሚሱም ቆስለዋል፤ ሱዳን ባልተገባ መልኩ የእርሻ መሬታችንን ወራብናለች” ማለታቸውን አስታውሶ ዘገባው አስፍረዋል፡፡

እንደ ፕሬስ ቲቪ ዘገባ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በእርሻ መሬቱ ጉዳይ እርስ በእርሳቸው ይወነጃጀላሉ፤ ኢትዮጵያም ሆነች ሱዳን የእርሻ መሬቱ የእኔ ነው የእኔ ነው ከመባባል ውጭ ከሰምምነት ላይ አልደረሱም፡፡

*********************************************************************

ዘጋቢ፡ ሸምሲያ አወል

ቀን 19/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply