የሱዳን የመረጃ ሚኒስትር ፋሰል ሳላህ ድንበራችን እስከ 70 ከመቶ አስመልሰናል ሲሉ ለሮይተርስ ተናገሩ፡፡          አሻራ ሚዲያ      ታህሳስ 18/2018…

የሱዳን የመረጃ ሚኒስትር ፋሰል ሳላህ ድንበራችን እስከ 70 ከመቶ አስመልሰናል ሲሉ ለሮይተርስ ተናገሩ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 18/2018…

የሱዳን የመረጃ ሚኒስትር ፋሰል ሳላህ ድንበራችን እስከ 70 ከመቶ አስመልሰናል ሲሉ ለሮይተርስ ተናገሩ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 18/2018 ዓ•ም ባህርዳር የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ግጭቱ የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች አይወክልም ሲል ነገሩን ዝቅ አድርጎ ተመልክቶታል፡፡ የሱዳን የመረጃ ሚኒስትሩ ፋሰል ሳላህ ከሮይተርስ ጋር ባደረጉት ቆይታ መከላከያ ሀይላችን መሬት እንዲያስመልስ ተልዕኮ ተሰጥቶታል፡፡ በእስካሁኑ ሁኔታውም እስከ 70% ድረስ መሬታችን አስመልሷል ያሉ። ሲሆን፣በኢትዮጵያ በኩል ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እንደወደመ የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳድር ማሳወቁን ቀደም ሲል አሻራ አሳውቋል፡፡ ሱዳን በካርቱም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሄዱበት ወቅት ንቀት እና እብሪት እንዳሳየች የአሻራ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ ሱዳን በግብፅ አይዞሽ ባይነት እና በኢትዮጵያ ባሉ ፅንፈኛ ሀይላት ድጋፍ ለወረራ ራሷን አዘጋጅታለች፡፡ በኢትዮጵያ ያሉ ፅንፈኞች ለመተከል ሰቆቃ ያጨበጨቡትን ያህል፣ ለሱዳን ወረራም እያጨበጨቡ ነው፡፡ ሱዳን የመተከል አማፂያን ሁሉ እያሰለጠነች ሲሆን፣ ግብፅ ደግሞ ከአሜሪካ የምታገኘውን የጦር መሳሪያ ለሱዳን እየሰጠች ነው፡፡ በዚህ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እብጠት የተሰማት ሱዳን መሬት የማግኛው ጊዜ አሁን ነው እያለች ነው፡፡ በኢትዮጵያ በኩል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቃልአቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ጉዳዮ ሱዳንን የሚመለከት ሳይሆን የታችኛውን መዋቅር ስህተት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ ነገር ግን የሱዳን የመረጃ ሚኒስትር ትናንትና ቅዳሜ ጉዳዮ የሱዳን የብሄራዊ ጥቅም ጉዳይ ነው ሲሉ ለእንግሊዙ ሮይተርስ ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡ በእርግጥ ችግርን አቃሎ መመልከት እና ቅብነት የብልፅግና ፖለቲካ መገለጫ በመሆኑ ነገርን ማቅለል አደጋ እንዳለው መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ሁሉ ውስብስብ ሁኔታ የማዕከላዊ መንግስትም ሆነ የአማራ ክልል በሁኔታው ልክ የተዘጋጁ አይመስሉም፡፡ የአዳሪዎች እና የደናቁራን ማህበር የሆነው የአማራ ብልፅግና በጃዊ እና በጓንጓ አካባቢ ጥበቃ የሚያደርጉ የፀጥታ ሀይላትን ሁሉ የመተከል ታጣቂዎች ላይ ጉዳት ታደርሳለችሁ ብሎ መልሷቸዋል፡፡ ብአዴን የሎሌነት ባህሪው እንዳለ ሆኖ ድንቁርናው ተጨምሮበት የሀገሪቱን እና የቀጠናውን ውስብስብ ሁኔታ ተረድቶ መፍትሄ ላያዘጋጅ ይችላል፡፡ ስለዚህ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ልሂቃን በተናበበ እና በተደራጀ መንገድ መፍትሄ መፈለግ እንደሚገባቸው የፖለቲካ ተንታኞች በአሻራ በኩል ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡ የሱዳን ወረራም ሆነ የህወሓት እብሪት መነሻው ከብልፅግና ጨቅላ የፖለቲካ መረዳት የተነሳ ነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ብልፅግና መሩ መንግስት በዓለም ፊት የተናቀ እና የተዋረደ መልክ ያለው ነው፡፡ ይሄን በመመልከትም ጎረቤት ሀገራት ለወረራ፣ ባለፀጋ ሀገራት የእርዳታ እጃቸውን ለማጠፍ ተዘጋጅተዋል፡፡ ኢ- መደበኛ ታጣቂዎች ደግሞ ንፅሃንን ለመግደል ቀስታቸውን ስለዋል፡፡ ከችግር በፊት ቀድሞ ተዘጋጅቶ መመከት የነቃ ማህበረሰብ እና ልሂቅ መገለጫው በመሆኑ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ተመካሪ ተግባር ሆኗል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply