የሱዳን ጦር በመተማ ወረዳ ቱመት መንዶካ ቀበሌ አንድ የላም እረኛን በማቁሰል የ4 ባለሀብቶችን 350 የቁም ከብቶችን ዘረፈ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም…

የሱዳን ጦር በመተማ ወረዳ ቱመት መንዶካ ቀበሌ አንድ የላም እረኛን በማቁሰል የ4 ባለሀብቶችን 350 የቁም ከብቶችን ዘረፈ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም…

የሱዳን ጦር በመተማ ወረዳ ቱመት መንዶካ ቀበሌ አንድ የላም እረኛን በማቁሰል የ4 ባለሀብቶችን 350 የቁም ከብቶችን ዘረፈ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ጎንደር ዞን ከመተማ ወረዳ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው የሱዳን ጦር ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ላይ አንድ የላም እረኛን በጥይት በማቁሰል 350 የቁም ከብቶችን ዘርፏል። ወራሪ ኃይሉ በዲሽቃ፣በብሬንና በመትረጊዬስ በመታገዝ ነው በተለያዩ ጊዜያት ጥቃት እና ዝርፊያ እየፈፀመ ያለው የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ መንግስት ዘንድ ተገቢ ምላሽ አልተሰጠውም ይላሉ ቅሬታ አቅራቢዎች። በቱመት መንዶካ ልዩ ስሙ መርትራድ 350 የቁም ከብቶች ከተዘረፉት መካከልም አቶ እምሩ ባዬ፣ ወንዳለና ሲሳይን ጨምሮ በድምሩ 4 የአካባቢው ባለሀብቶች ናቸው። ቅሬታ አቅራቢዎቹ “ፍትህ እንፈልጋለን፤ መንግስት ካለ ይስማን ሀገር እየተደፈረና እየተዘረፈ ነው” ሲሉ ተማፅነዋል። ከሳምንታት በፊት 5 ኢትዮጵያዊያን የቀን ሰራተኞች ለሱዳን በመረጃ ምንጭነት በሚያገለግሉት ፈላታዎች መገደላቸውን ምንጮችን ዋቢ በማድረግ መዘገባችን ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply