የሱዳን ጦር ከእለት ወደ ከእለት የኢትዮጵያን ሉአላዊነትን በመጋፋት በዲሽቃ በመታገዝ ቃጠሎ እና ዝርፊያ ከመፈፀም አለመታቀቡን የመተማ እና የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ።…

የሱዳን ጦር ከእለት ወደ ከእለት የኢትዮጵያን ሉአላዊነትን በመጋፋት በዲሽቃ በመታገዝ ቃጠሎ እና ዝርፊያ ከመፈፀም አለመታቀቡን የመተማ እና የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ።…

የሱዳን ጦር ከእለት ወደ ከእለት የኢትዮጵያን ሉአላዊነትን በመጋፋት በዲሽቃ በመታገዝ ቃጠሎ እና ዝርፊያ ከመፈፀም አለመታቀቡን የመተማ እና የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የሱዳን ጦር ከእለት ወደ ከእለት የኢትዮጵያን ሉአላዊነትን በመጋፋት በባለሀብቶችና አርሶ አደሮች ላይ በዲሽቃ በመታገዝ ቃጠሎና ዝርፊያ ከመፈፀም አለመታቀቡን ነው የመተማ እና የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ነዋሪዎች ለአሚማ የገለፁት። የሱዳን ጦር በተለይም በመተማ እና ምዕራብ አርማጭሆ አዋሳኝ በበረከት ስናር በተባለ የእርሻ ልማት አካባቢ በየቀኑ ዲሽቃ፣ ብሬንና መሰል የቡድን መሳሪዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያን ባለሀብቶችንና አርሶ አደሮችን እያሳደዱ መሆኑ ተገልጧል። እንደአብነትም ከሳምንታት በፊት በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በስናር የእነ አቶ አሰማራው መኮንን እና ከቀናት በፊት ደግሞ የእነ ባሻ ጥጋቡን ካምፕን ሱዳኖች መያዛቸው የተገለፀ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ የመተማ ባለሀብት የሆኑትን የእነ አቶ መልካሙ እና ወ/ሮ ለምለም የእርሻ ካምፕን በመቆጣጠር ዝርፊያ እና ቃጠሎ መፈፀማቸው ተነግሯል። የማሽላ ማራገፊያ ማሽኖችን/ደጋጋዎችን/ ዘርፈው ከመውሰዳቸውና ካምፕ ከማቃጠላቸው ባሻገር በአካባቢው ሰፍረው እንደሚገኙ ነው የደረሰን መረጃ ያመለከተው። የወ/ሮ ለምለምን ካምፕ ትናንት ታህሳስ 29 ቀን፣ የአቶ መልካሙን የእርሻ ካምፕ ደግሞ ዛሬ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓም በዲሽቃ ተኳሹ የሱዳን ጦር መያዙን ነው የመተማና የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ነዋሪዎች የገለፁት። በስናር ሰፊ የእርሻ ልማት ያላቸው አቶ መልካሙ ከሀገረ እስራኤል ተመልሰው በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ በእርሻ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ሲሆኑ ወ/ሮ ለምለምም ደግሞ በእርሻ ልማት ከተሰማሩትና በትሕነግ ከፍተኛ ጫና ሲደርስባቸው ከነበሩ የወልቃይት አማራ ባለሀብቶች መካከል አንዷ መሆናቸው ተገልጧል። የመንግስት ዝምታ የሚሰበረው ሱዳን እስከየት ሲደርስ ነው? ያሉት ነዋሪዎቹ በውይይት ይፈታል ከተባለም የሱዳን ጦር በየቀኑ ሉአላዊነትን እየተጋፋ፣ እየተስፋፋና እየዘረፈ ነው ወይ? ሲሉ በግርምት ጠይቀዋል። ፎቶ: ፋይል

Source: Link to the Post

Leave a Reply