የሱዳን ጦር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ገብቶ ከአንድ ቢሊየን  ብር በላይ የሚገመት ንብረት አወደመ፡፡       ( አሻራ  ታህሳስ 18፣ 2013 ዓ.ም ባህርዳር)  … የሱዳን ጦር ከጥቅምት 27…

የሱዳን ጦር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ገብቶ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት አወደመ፡፡ ( አሻራ ታህሳስ 18፣ 2013 ዓ.ም ባህርዳር) … የሱዳን ጦር ከጥቅምት 27…

የሱዳን ጦር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ገብቶ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት አወደመ፡፡ ( አሻራ ታህሳስ 18፣ 2013 ዓ.ም ባህርዳር) … የሱዳን ጦር ከጥቅምት 27 ቀን 2013ዓ.ም ጀምሮ በመካናይዝድ ጦር በምዕራባዊ የጎንደር የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ ለአንድ ወር የዘለቀ ጥቃት ከፍቷል፡፡ በዚህም 500 የሚደርሱ አባዎራዎች ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ፣በድምሩ ሁለት ሺ ኢትዮጵያውያን ከግዛታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በከባድ መሳሪያ በተደራጀ ሁኔታ የተከፈተው ጥቃት ዛሬም እንዳልቆመ የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር አሳውቋል፡፡ ዞኑ እንደገለፀው የሱዳን ጦር ክፉኛ እየተስፋፋ ሲሆን ማዕከላዊ መንግስቱ እስካሁን የሰላም አማራጭን አቅርቧል፡፡ በቅርቡም በአዲስ አበባ ድርድር እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡ በካርቱም የተደረገው ድርድር ስምምነት አልባ እንደነበር አሻራ ሰምቷል፡፡ የኢትዮጵያ ጦር ጥቅምት 25 ቀን 2013 በህወኃት ላይ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ሲወስድ፣ የሱዳን ሀይል ደግሞ በአንፃሩ ኢትዮጵያን መውጋት ጀምሯል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአብዮ እና በዳርፉር ግዛቶች ሰላም በማረጋጋት እና በሶማሊያ የአልሸባብን ሽብር በመግታት በቀጠናው ሰፊ ሚና እንዳለው ይታወቃል፡፡ ሱዳን ግን ይሄን ሁሉ ፖለቲካዊ ውለታ በመዘንጋት የግብፅን ፍላጎት ተከትላ በኢትዮጵያ ወረራ እየፈፀመች ነው፡፡ ንብረት እየዘረፈችም ነው፡፡ አሁን ባለው የሀይል አሰላለፍ ልዮነት ምክንያት ሱዳን በአሜሪካ አደራዳሪነት ከግብፅ ጎን የቆመች ሲሆን፣ ግብፅም በሱዳን የጦር ልምምድ እያደረገች እንደሆነ የቻይናው ሲቲጂኤን ጂ ዘግቧል፡፡ ከዚህ ቀደም ሱዳን ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ የህወኃት እና የጀብሃ የመገንጠል አራማጆች ምሽግ የነበረች ሲሆን ከድህረ 1983 ወዲህ ግን ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር መልካም የሚባል ግንኙነት ነበራት፡፡ የኢትዮጵያ መሪዎች ያልተሰመረ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ እና የብልፅግና ቁንጮዎች በጎጥ እና በብሄር ሽኩቻ ገብተው ሀገራዊ አንድነትን ማላላታቸው ሱዳን እንድትወር ገፋፍቷታል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply