የሱዳን ጦር የኢትዮጲያን ድንበር አልፎ  መግባቱን አሁንም  አላቆመም፡፡        (ታህሳስ 21፣፡2013 ዓ•ም ) የኢትዮጲያን ሉዓላዊነት በመጣስ ወደ ኢትዮጺያ የገባው የሱዳን ጦር ከባድ…

የሱዳን ጦር የኢትዮጲያን ድንበር አልፎ መግባቱን አሁንም አላቆመም፡፡ (ታህሳስ 21፣፡2013 ዓ•ም ) የኢትዮጲያን ሉዓላዊነት በመጣስ ወደ ኢትዮጺያ የገባው የሱዳን ጦር ከባድ…

የሱዳን ጦር የኢትዮጲያን ድንበር አልፎ መግባቱን አሁንም አላቆመም፡፡ (ታህሳስ 21፣፡2013 ዓ•ም ) የኢትዮጲያን ሉዓላዊነት በመጣስ ወደ ኢትዮጺያ የገባው የሱዳን ጦር ከባድ መሳሪያዎችን ጨምሮ በማስጠጋት ላይ እንደሆኑም የአሻራ ሚዲያ የመረጃ ምንጮች ተናግረዋል። ጉዳዩን በቸልተኝነት እያየ ያለው መንግስትም የተወሰኑ ከባድ ነሳሪያዎችን ከማስጠጋት በቀር ወደ ቦታው የሄደ የመከላከያ ሰራዊት አባል አለመኖሩን ተከትሎ የሱዳን ጦር የልብ ልብ እንደተሰማቸውም አክለው ገልፀውልናል። በአካባቢው ያለው የአማራ ልዩሐይል መሆኑን ያዩ የአካባቢው ማህበረሰብ የፌደራል መንግስቱ ጉዳዩን በቸልተኝነት እያየ እና የሀገሪቱን ዳር ድንበር በአማራ ልዩሐይል የማስጠበቅ ሴራ ላይ እንዳለ ያሳያልም ሲሉ ገልፀውልናል። ወደ ኢትዮጲያ 30 ኪ.ሜ የገባው የሱዳን ጦር እና የአማራ ልዩ ሀይል በቅርብ እርቀት ላይ የሚተያይ ሲሆን እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የተኩስ ልውውጥ እንደሌለም ነው የገለፁት። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ የዲፕሎማሲ ትግል እያደረግሁ ነው ብሏል፡፡ ከሱዳን ጀርባ ግብፅ እንዳለች መንግስት እየገለፀ ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply