የሱዳን ጦር የኢትዮጲያን ድንበር ጥሶ በመግባት የባለሀብቶችንና የአርሶ አደሮችን ንብረት እየዘረፈ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡                አሻራ ሚዲያ…

የሱዳን ጦር የኢትዮጲያን ድንበር ጥሶ በመግባት የባለሀብቶችንና የአርሶ አደሮችን ንብረት እየዘረፈ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ…

የሱዳን ጦር የኢትዮጲያን ድንበር ጥሶ በመግባት የባለሀብቶችንና የአርሶ አደሮችን ንብረት እየዘረፈ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም መንግስት በካሃዲው ትህነግ ላይ እርምጃ መወሰዱን ተከትሎ የሱዳን ጦር በምዕራብ አርማጭሆ እና በመተማ ኃይሉን በማስጠጋት ምሽግ ሲቆፍር እና በባለሀብቶች ላይ ጉዳት ሲያደርስ መቆየቱ ይታወሳል። የመንግስት ዝምታ የልብ ልብ የሰጠው የሱዳን መከላከያ ሰራዊት ከሰሞኑም በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በአብደራፊ በኩል ሰላም በር እና በጠረፍ ወርቅ ቀበሌ ስናር እና መሰረት መቅረጫ አካባቢ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመዳፈር ከባድ መሳሪያ ጭምር በባለሀብቶችና አርሶ አደሮች ላይ በመተኮስ የእርሻ ካምፖችን በመቆጣጠር የለየለት ዘረፋ ውስጥ መግባቱን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው። ይህ የሱዳን የወረራ አካሄድ መንግስት ከትህነግ ጋር በነበረው ጦርነት ተዳክሟል፣ ጦር የለውም ብለው የነገሯቸውን የተሳሳተ መረጃ ከመስማታቸው ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ የገለፁት በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ናቸው። ነዋሪዎች እንደገለፁት አሁን ላይ በመንግስት በኩል ለሱዳን ጦር ተገቢ የአፀፋ ምላሽ እየተሰጠ አይደለም። በዚህም አብደራፊ አካባቢ በሰላም በር፣ በመሰረት መቅረጫና በስናር በኩል ተጨማሪ ኃይል በማስጠጋት በበርካታ ባለሀብቶችና አርሶ አደሮች የእርሻ ካምፕ ላይ የቡድን መሳሪያዎችን ጭምር በመተኮስ ዓመቱን ሁሉ የደከሙበትን የደረሰ ሰብል እንዳይሰበስቡ አድርገዋል፤ ቦታውን በመቆጣጠርም በጎን ተሽከርካሪ አቅርበው እየጫኑ ወደ ሱዳን እየወሰዱ መሆናቸውም ነዋሪዎች ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply