የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት በምዕራብ አርማጭሆ በድጋሚ ጥቃት እየፈጸመ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡               አሻራ ሚዲያ…

የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት በምዕራብ አርማጭሆ በድጋሚ ጥቃት እየፈጸመ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ አሻራ ሚዲያ…

የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት በምዕራብ አርማጭሆ በድጋሚ ጥቃት እየፈጸመ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡- 16/04/ 2013ዓ.ም ባህርዳር ቀደም ሲል የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት በአብርሀጅራ ወረዳ በስናር የእርሻ ልማት ካምፕ ውስጥ ጥቃት መፈጸሙን መግለጻችን ይታወሳል፡፡ በዚህም የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት የተለያዩ ንብረቶች እንደወደሙ ገልጸው በግምት ሁለት ሚሊዮን ብር የሚሆን ንብረት ማውደሙን መግለጻችንም የቅርብ ግዜ ትውስታ ነው፡፡ የተለያዩ የእርሻ መሳሪያዎች ትራክተር፣ጀኔኔተር፣የሰብል መርጫ እና ሌሎች የሰብል ምርቶች እንደተቃጠሉባቸውና እንደተዘረፉባቸውም ገልጸውልን ነበር፡፡ በአሁኑ ሰዓትም የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት በምዕራብ አርማጭሆ አብደራፊ አካባቢ ጥቃት እየፈጸመ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ ነዋሪዎች እንደገለጹት የሱዳን የጦር ሀይል በምዕራብ አርማጭሆ በአካባቢያ በመግባት የደፈጣ ውጊያ እያደረገብን ይገኛል እኛም ስንለፋበት እና ስንደክምበት የቆየነውን ሰብል ትተን እየሸሸን እንገኛለን የሱዳን ጦርም ዝርፊያ እያካሄደ ነው ብለዋል የመረጃ ምንጫችን፡፡ ስለሆነም የከፋ ችግር ከመድረሱ በፊት መንግስት አስፈላጊውን ጥበቃና እርምጃ ይውሰድልን ለተበደልነውም መንግስት ካሳ ይክፈለን ሲሉ ምንጫችን ተናግረዋል፡፡ እንደምንጫችን ገለጻ መንግስት የሱዳን ጦርን በችልተኝነት በማለፉ ጦሩ ያለማንም ከልካይ ብዙ ግፍና በደል እያደረሰብን ይገኛል ብለዋል ፡፡ በመጨረሻ ለሚመለከተው የመንግስት አካላት ብናመለክትም ምንም ሊሰማን የሚችል አካል አላገኘንም ብለዋል ምንጫችን፡፡ ስለሆነም በአሁኑ ሰዓት ችግር ውስጥ ስለምንገኝ መንግስት በአስቸካይ ይድረስልን ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply