የሱዳን ፀጥታ ኃይሎች በተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጋዝ ተኮሱ

https://gdb.voanews.com/09680000-0a00-0242-b632-08da67e943c7_w800_h450.jpg

በሱዳን ያለውን ቀውስ ለማስቆም በሚል በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ አገሪቱን በሚመሩት ጄኔራሎችንና ተቃዋሚ ድርጅቶች መካከል የተደረሰውን ስምምነት በመቃውም ካርቱም ውስጥ ሰልፍ በወጡ ነዋሪዎች ላይ የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጋዝ ተኩሰዋል። 

በሺህ የሚቆጠሩ የዲሞክራሲ አቀንቃኞች ዛሬ በካርቱም ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ በሲቪሎች ከሚቋቋም መንግስት ውጪ ሌላ አማራጭ እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል ሲል የኤ.ኤፍ.ፒ ዜና ወኪል ዘግቧል።

የዛሬው ተቃውሞ የተካሄደው አገሪቱን ለረጅም ዘመን በገዙት ኦማር አልበሽር መንግስት ላይ ተቃውሞ የተጀመረበት አራተኛ ዓመትን ለማሰብም ነው ተብሏል። እርሳቸውን የተካውን ሲቪል የሽግግር መንግስት በአብደል ፈታህ አል-ቡርሃን የተመራ መፈንቅለ መንግስት ባለፈው ዓመት አፍርሶታል። 

አል-ቡርሃን ስልጣኑን ከያዙ ጀምሮ ሱዳን በየሳምንቱ ተቃውሞ በማስተናገድ ላይ ነች። በዚህ ተቃውሞ እስከ አሁን ቢያንስ 122 ሰዎች ሲገደሉ በሺህ የሚቆጠሩ ጉዳት እንደደረሰባቸው ይነገራል። 

Source: Link to the Post

Leave a Reply