የሱፍ ኢብራሂም የአብን ም/ሊቀመንበር “የጥላቻ ጥብቆ በማልበስ የአንድን ህዝብም ይሁን ሀገር ዘላቂ ጥቅምና ደህንነት ማረጋገጥ እንደማይቻል በግልፅ መነገር አለበት” አሉ፡፡…

የሱፍ ኢብራሂም የአብን ም/ሊቀመንበር “የጥላቻ ጥብቆ በማልበስ የአንድን ህዝብም ይሁን ሀገር ዘላቂ ጥቅምና ደህንነት ማረጋገጥ እንደማይቻል በግልፅ መነገር አለበት” አሉ፡፡…

የሱፍ ኢብራሂም የአብን ም/ሊቀመንበር “የጥላቻ ጥብቆ በማልበስ የአንድን ህዝብም ይሁን ሀገር ዘላቂ ጥቅምና ደህንነት ማረጋገጥ እንደማይቻል በግልፅ መነገር አለበት” አሉ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 01 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን ም/ሊቀመንበር አቶ የሱፍ ኢብራሂም በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያጋሩት መልዕክት የሚከተለውን ብለዋል፡፡ ፅንፈኛውን የሸኔ ገፅታ ካልተላበስን ተመራጭ አንሆንም የሚል ሀሳብ ይኖራል። አጋጣሚው ሲገኝ ኦነግ ነኝ የሚሉት በምክንያት ነው። ብዙዎቹ ንግገራቸውን የሚጀምሩት ኦነግ ነበርን እያሉ ነው። “ቀደም ሲል ኦነግ ሸኔን እደግፍ ነበር” የሚሉ በርካቶች ናቸው። ያለፈ ተሳትፏቸውን በማስታወስ ለአሁን ፍጆታቸው ይጠቀሙበታል። ታየ ደንደአም መናገር ሲጀምር “የኦነግ አባል ነበርኩ”ይላል። ዛሬ መሀል ሜዳ ሚዲያ ላይ ቀርቦ ሲናገር “ኦነግ ነበርኩ” የሚለውን በመግቢያነት ሲያቀርብ ሰምተናል። በያዙት ግዛት ውስጥ ያሉትን የመብት ጥያቄዎች ባግባቡ ሳይመልሱና ዝቅተኛውን የመኖር መብት እንኳ ሳሳያከብሩና ሳያስከብሩ ተጨማሪ ኬኛ ማለት ፈንጅ ከመጨበጥ የተለየ ትርጉም የለውም። ሆኖም አማራ ጠል ትርክቱና በርካታ መገለጫዎቹ ገና ወደፊት በሰፊው ተጠናክረው በይፋ አይቀርም። በርግጥ የቆየ ምግባራቸውን አሁን መሬት ላይም እንደጀመሩ መረጃዎች ያሳያሉ። በኦሮሚያ የሚኖረውን አማራ የመግፋትና የማሸማቀቅ እንቅስቃሴዎች እየተበራከቱ መጥተዋል። በየቀኑ መረጃዎች ይደርሱናል። የነ ታየ ደንደአ ንግግር ለዚህ የተላለፈ መልእክት ነው! ልዩነታቸው ጥሬ የስልጣንን በተመለከተ ብቻ እንደሆነ እናውቃለን። ሰፊውንና የሀገራችን አንድ ወሳኝ አካል የሆነውን የኦሮሞ ህዝብ የሰላም፣ የፍትህ፣ የእኩልነትና የልማት ተጠቃሚ እንዲሆን ከማስቻል ይልቅ ራሱንና ያለውን እንዲዘነጋ በማድረግ ሌሎች ወገኖቹን በጥላቻና በጥርጣሬ እንዲመለከትና ሌሎችም እንዲጠራጠሩት የሚያደረግ ድንክ ፖለቲካ በቃ ሊባል ይገባዋል። የጥላቻ ጥብቆ በማልበስ የአንድን ህዝብም ይሁን ሀገር ዘላቂ ጥቅምና ደህንነት ማረጋገጥ እንደማይቻል በግልፅ መነገር አለበት። በምኞት ያደረው ሁሉ መሳካት እንደማይችል መገንዘብ ብልህነት ነው። ሀምሳ አመታት የቆየ አጉራ ዘለል የትርክት ፈብራኪ ትቢያ የሆነው በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንደሆነ አንጋቢዎቹ ጭምር የታደሙት እውነታ ነው! ባጠቃላይ የሰሞኑ ጉዳይ ከፍ ያለ ጭብጥ ይኖረዋል ከተባለ በሀገራዊ የሀይል አሰላለፉ ውስጥ እኛ ብቻ ነን የበላይ አስፈፃሚዎች የሚል አጀንዳ ለመቅረፅ ይመስላል። እኛ ብዙ ስራ አለብን! አማራዊ አንድነታችን የትግላችን አምድና የስኬታችን ዋልታ ስለሆነ ማጠናክር አለብን።ከሀገር ወዳድ ሀይሎች ጋር በጎ ጥምረት በመፍጠር ፍትህና እኩልነትን ለማንገስ መረባረብ ይገባናል። በሁሉም ጎራ የተሰለፈ የአማራ ፖለቲከኛ መገንዘብ ያለበት—እንደ ግለሰብም ይሁን እንደ ቡድን የምንመኘውን አሟልተን ለማሳካትና ዘላቂ ለማድረግ እንደህዝብ በአንድነት መቆም ግደታ መሆኑን ነው። የአማራ ህዝብን አደረጃጀትና ትግል ለንጥል አጀንዳዎች ማስፈፀሚያ መድረክ ለማድረግ ከፈለግን ሁላችንም በምንዝር ከተጎጅነት አናመልጥም ። እንደህዝብ ተገፍተንና ተጠቅተን እንደ ግለሰብ ክብር ልንጎናፀፍ አንችልም! እኩልነትን የማይፈልጉ ስብስቦች አካባቢያቸውን አዛብተው ሲያበቁ ተጨማሪ ቀጠናዎችን እንደሚቧጭሩ በተደጋጋሚ ተመልክተናል። እነዚህ ሰዎች እውቅናና ክብር የሚሰጡት ለሰው ልጅ ሳይሆን ለጅረትና ጨፌ መሆኑን እናውቃለን። ፍትህና እኩልነት ለሚያቅረው ሰው መድሀኒቱ የህግ የበላይነት ቢሆንም አፈፃፀሙ ቀላል አይደለም። የብልፅግና ፖርቲ በነታየ ደንደአ ላይ ህጋዊ ወይም ፖለቲካዊ ርምጃ ይወስዳል ተብሎ አይጠበቅም። አማራዊ የባህል ህግጋትን መሰረት በማደረግ ካሁን በፊት ያላግባብ የተቸሩ ካባዎችን እንዳልተሰጡ መቁጠር ይቻላል። ህዝባችንን የማይወዱ ሆነው ካባ የደረሳቸው ሰዎች በጃቸው ያለው “ጨርቅ ብቻ” እንደሆነ ሊዘነጉት አይገባም። በመጨረሻ ከታየ ደንደአ ጀርባ ማን ሊኖር ይችላል? የሚለውን ጥያቄ ማንሳቱ አይከፋም! ከተወሰኑት የሚከተለውን አደረግሁ ባቸው። ግን ዪትዩቡ ሪዳይሬክት አያረግም ዘወትር አዳዲስ መረጃ እንዲደርስዎ https://t.me/asharamedia24 በመጫን ይቀላቀሉን። ዩትዩብ፥ https://bit.ly/33XmKro ላይክ እና ሰብስክራይብ ያድርጉን ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply