የሲሚንቶ ምርቶችን በህገወጥ መንገድ እየወሰዱ ለገበያ የሚያቀርቡ ተቋራጮች ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነ ተገለጸ፡፡

ለመንግስት ትልልቅ ተቋማት ግንባታ እና እድሳት የሚቀርበው የሲሚንቶ ምርትን ተደራሽ ለማድረግ ከመንግስት በቀጥታ የማቅረብ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ለመንግስት ተቋማት ግንባታ የሚውል የሲሚንቶ ምርት አቅርቦት በቀጥታ ከአምራቾች እንዲያገኙ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ለአነስተኛ ጥገናዎች ከመንግስት ልማት ድርጅቶች እና ከአቅራቢዎች እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ እሸቴ አሰፋው ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

ከመንግስት ተቋማት በኩል ዩኒቨርስቲዎች፣ የጤና ተቋማት እና ሌሎችም ተቋማትም አቅርቦቱን እያገኙ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የመንግስት ተቋማት ላይ የሚደረጉ ግንባታዎች በሲሚንቶ ምርት እጥረት ምክንያት እንዳይቋረጡ የሚሰራው ስራ ስኬታማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ምንም ዓይነት የሲሚንቶ እጥረት እንደሌለ የገለጹት ሚኒስትር ዲኤታው በመንግስት ስም የሲሚንቶ ምርቶችን እየወሰዱ በህገወጥ መንገድ ለገበያ የሚያቀርቡ ተቋራጮች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

ለዚህም የማስተካከያ ስራ ለመስራት ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

ቀን 17/07/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply