የሲሚንቶ ዋጋ በድጋሚ በነጻ ገበያ እንዲመራ ተወሰነ

ካለፈው ሐምሌ ወር መጀመሪያ ጀምሮ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ዋጋ ሲወንስለት የነበረው የሲሚንቶ ገበያ፤ ከነገ ጀምሮ በነጻ ገበያ እንዲመራ ተወሰነ። አዲሱ ውሳኔ፤ በፋብሪካዎች መካከል ያሉትን አከፋፋዮች እኛ ቸርቻሪዎችን፤ ከሲሚንቶ ገበያ ስርዓት እንዲወጡ ያደረገውን አሰራር የቀለበሰ ነው። 

ላለፉት አምስት ወራት በስራ ላይ በነበረው አሰራር መሰረት፤ የሲሚንቶ አከፋፋዮች የሚመረጡት በክልል እና በከተማ አስተዳደሮች አማካኝነት ነበር። አሁን ይፋ የተደረገው አዲስ መመሪያ በአንጻሩ፤ ፋብሪካዎች “የሲሚንቶ ምርቱን ተደራሽ ያደርጉልኛል” የሚሏቸውን አከፋፋዮች ራሳቸው እንዲመርጡ ነጻነት የሰጠ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ተሻለ በልሁ ዛሬ ታህሳስ 13፤ 2015 በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

[ይህ ዘገባ ተጨማሪ መረጃ ይታከልበታል]

The post የሲሚንቶ ዋጋ በድጋሚ በነጻ ገበያ እንዲመራ ተወሰነ appeared first on Ethiopia Insider.

Source: Link to the Post

Leave a Reply