የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ከፍሪደም ሀዉስ ጋር በመተባበር የሲቪክ ማህበራት አካዳሚክ ትብብር አወደ ጥናት እያካሄደ ይገኛል። “የሲቪል ማህበረሰብ የምሁራን ትብብር ለተሻለ የሰበዓ…

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ከፍሪደም ሀዉስ ጋር በመተባበር የሲቪክ ማህበራት አካዳሚክ ትብብር አወደ ጥናት እያካሄደ ይገኛል።

“የሲቪል ማህበረሰብ የምሁራን ትብብር ለተሻለ የሰበዓዊ መብት ጥበቃ እና ዲሞክራሲ ስርዓት” በሚል መሪ ቃል፣የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ከፍሪደም ሃዉስ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት አዉደ ጥናት ዛሬ 23/2016 ዓ.ም ተካሂዷል።

የመድረኩ ዓላማም የሲቪል ማህበረሰብ እና የአካዳሚክ ትብብር ማስተዋወቅ ዋነኛዉ ዓላማዉ መሆኑን የምክርቤቱ ተወካይ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሀና ወልደገብርኤል ተናግረዋል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ከተቋቋመበት ግዜ አንስቶ አካታች በሆነ መንገድ የተለያዩ የባለድርሻ አካላትን በመለየት፣በጋራ ሊሰሩ የሚችሉትን ስራዎች በጋራ በመለየትና በመመካከር በአጋርነት መንፈስ ሲሰራ መቆየቱን ዳይሬክተሯ ገልፀዋል።

ምክር ቤቱ ከፌዴሽን ምክር ቤት፣ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መፈራረሙ የተገለፀ ሲሆን፣ በቅርቡም ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ከኢትዮጵያ ተሀድሶ ኮሚሽን ጋር ስምምነት በመፍጠር በጋራ ለመስራት ማቀዱን አስታዉቋል።

የአካዳሚክ እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጊቶች የተለያየ ጥንካሬ እና እዉቀት ያላቸዉ ዘርፎች እንደመሆናቸዉ፣ በሀገር ሰላም፣ልማትና ዲሞክራሲ ዕድገት ላይ ላቅ ያለ አስተዋጽኦ በማበርከት አዎንታዊ የማህበረሰብ ለዉጥ እንዲመጣ ያስችላል ተብሏል።

ይህ ትበብር በሰብዓዊ መብት እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰቦች እና የአካዳሚክ ትብብር መሆኑን የገለፁት የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የህግ እና ፖሊሲ አማካሪ አቶ ዘላለም እሸቱ፣ በቀጣይ ከሌሎች የሲቪል ማህበረሰቦች ጋር በጋራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

አቶ ዘላለም አክለዉም ይህ ትብብር አዲስ የስራ ባህል በመፍጠር ለዲሞክራሲ በተለይም ሰብዓዊ መብት ላይ በጋራ ለምስራት የሚያስችል መሆኑን እስታዉቀዋል።

ሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. የምክክር መድረክ መባዘጋጀት ከሲቪል ማህበረሰብ እና ምሁራን የተውጣጡ ዘጠኝ አባላትን ያካተተ ቋሚ የትብብር ኮሚቴ መዋቀሩ ይታወሳል።

በዛሬዉ መድረክ ላይም ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ምሁራኑን ጨምሮ ከምርምር ማዕከላት፣ ከመንግስት ተወካዮች፣ ከሚዲያ፣ የዴሞክራሲ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ እካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

በአቤል ደጀኔ
መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply