የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ 6 ወራት ጊዜ ውስጥ ከ3መቶ ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ አግኝቻለሁ አለ።የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ወደ ው…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/LrfahwwggHyojBQAeUN7NnqPIOPj2qQv1em0bdnTs280ikniPmEyM7hyS1kt1hFUCBGL8kMDYJ_qO1JHRwpZoSYeSGxpPI4_Q2kds_t311C3SM76BylQcprN3gYMMCELegjNwJlxd5xHK25CfoF7bJid_zSpjapj6g2zkyXjLvjoQW21M50_R8xS1ToAnK6z2JQr41_8FqGFTRkYoWeHGw6jqJfPI9KtIDmV_xm7jWWC0THRZe1KfAVPFJCbQqoG37-3v0EEQpSNpTTr6_a5a04Km-zWYQAmqfgeAHmQT6Ohvp5GsIBpKqVmL7D3QIrQml6yMNTp41N_2B4sHacbRA.jpg

የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ 6 ወራት ጊዜ ውስጥ ከ3መቶ ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ አግኝቻለሁ አለ።

የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ወደ ውጭ ከተላከ የአቮካዶ ዘይት እና የተቀነባበረ የወተት ምርት ከ3መቶ38ሺህ ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል።

በፓርኮቹ ውስጥ የሚገኙት ፋብሪካዎች በአቅርቦት ሰንሰለቱ እና በአገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ ባይሆንም ይህን ያህል ገቢ ተገኝቷል ብሏል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት እና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጴጥሮስ ማርቆስ፤ ለአገር ውስጥ ገበያም ሆነ ለውጭው በማቅረብ ሶስት ኩባንያዎች ለገቢው መገኘት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል ነው ያሉት።

በአሁኑ ሰዐት ከአገር ውስጥም ከውጭም ባለሀብቶች ወደ ፓርኩ ገብቶ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀው ፤ እስከ አሁን ድረስም ወደ 28 አከባቢ ፕሮጀክቶች ጋር ውል ተፈራርመናል ብለዋል።

የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለ3መቶ12 ሰራተኞች ቋሚ የስራ ዕድል እና ለ6መቶ32 ሰራተኞች ደግሞ ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠሩንም ዳይሬክተሩ ነግረውናል።

በእስከዳር ግርማ
የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply