የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት ምሥረታ 2ኛ ዓመት እየተከበረ ነዉ

ሰኞ ሰኔ 27 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት 2ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በሐዋሳ ከተማ ሲዳማ ባሕል አዳራሽ መከበር ጀምሯል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የክልሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይም የሲዳማ ሕዝብ ራሱን በራሱ ለማስተዳደርና የመልማት ጥያቄን በማንገብ ለዘመናት ባደረገዉ መራር ትግል የተገኘዉን ድል ልማትና መልካም አስተዳደርን በማስፈን ለመድገም የክልሉ መንግሥትና ሕዝብ ተቀናጅቶ እየሠራ እንደሆነም መጠቆሙን ኢፕድ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply