የሲዳማ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተመሠረተ

የሲዳማ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተመሠረተ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰባት አባላት ያሉት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በመምረጥ ተመሠረተ።
ጉባኤው የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሀዋሳ ከተማ በሠላም ግንባታ ዙሪያ ለሁለት ቀናት ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ ነው፡፡
የተመሠረተው ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት ወንጌላዊ ተክሉ ዳኮሌ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአዲስ መልክ በተደራጀው ክልል ጉባኤው እንዲመሠረት በማድረጉ ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ጉባኤው በሃገር ሠላምና ልማት ጉዳይ ከመንግስት ጎን በመሆን እንደሚሠራም ነው ያስታወቁት፡፡

The post የሲዳማ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተመሠረተ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply