የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ፣ በሕልውናዬ ላይ የተደቀኑ ችግሮች ካልተፈቱ ከአገራዊ ምክክር ሂደቱ ልወጣ እችላለኹ ሲል ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጻፈው አቤቱታ አስጠንቅቋል።

ፓርቲው በመስከረም ወር ከኮሚሸኑ ጋር አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ከተፈራረመ ወዲህ፣ የሲዳማ ክልል መንግሥታዊ አካላትና ምርጫ ቦርድ በሕልውናው ላይ አደጋ ላይ እንደደቀኑበት ገልጧል።

ፓርቲው፣ በአመራሮቹና አባሎቹ ላይ የሚደርሰውን እስር፣ ወከባና የዋና ቢሮውን ቁልፍ በዲስፕሊን ለታገዱ አመራሮች ተላልፎ በመሰጠቱ ዙሪያ፣ ለክልሉ ፍርድ ቤትና ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ ቢያቀርብም፣ መፍትሄ አለማግኘቱም ገልጧል።

የምክክር ኮሚሽኑ፣ አመራሮቹ እንዲፈቱ፣ ዋና ጽሕፈት ቤቱ እንዲመለስለትና የምርጫ ቦርድን አካሄድ እንዲያስቀይርለትም ፓርቲው ጠይቋል።

መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply